የኢለን መስኩ ቴስላ ኩባንያብየሰራው ፈጣኑ ቻርጀር 15 ደቂቃ ይፈጅ ነበር
የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪን በአራት ደቂቃ የሚሞላ ቻርጀር ተሰራ።
በዓለማችን ለይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት እና ምርት እየጨመረ ይገኛል፡፡ ይሁንና እነዚህን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንደ ልባቸው ሊስተናገዱበት የሚችሉት ቻርጀር ማግኘት አደጋች ሆኗል፡፡
ሌላኛው አስቸጋሪ ነገር ደግሞ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ለማድረግ የሚፈጀው ጊዜ ረጅም መሆን ሲሆን በየጊዜው እየተሸሻለ በመምጣት ለይ ይገኛል፡፡
የእንግሊዙ ኒዮቦልት የቴክኖሎጂ ኩባንያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በቶሎ ቻርጅ ለማድረግ መላ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡
ኩባንያው እንግዶች በተገኙበት በአራት ደቂቃ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪን እንደሚሞላ አረጋግጧል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የአሜሪካው ፎርድ ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና የማምረት እቅዱን አራዘመ
በስፖርት ተሽከርካሪ ላይ የተሞከረው ይህ የባትሪ ቻርጀር በአራት ደቂቃ ውስጥ 80 በመቶ እና ከዛ በላይ መሙላት የቻለ ሲሆን በቅርቡ ተጨማሪ ሙከራዎችን እና ማሻሻያዎችን በማድረግ ለገበያ እንደሚውል አስታውቋል፡፡
አሁን ላይ የኢለን መስኩ ቴስላ ኩባንያ ይፋ ያደረገው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ መሙያ ጊዜ ከ15-20 ደቂቃ ይፈጃል፡፡
የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባያዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ የሚሞላበትን ጊዜ ለማሳጠር በሙከራዎች ላይ ሲሆኑ የዓለም ገበያን እየተቆጣጠሩ የመጡት የቻይና ኩባንያዎች አዲስ ፈጠራ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃሉ፡፡