በኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ብቻ 183 ሰዎች በኮቪድ 19 ህይወታቸውን አጥተዋል
በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 208 ደርሷል
ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
በኢትዮጵያ ባለፉት 7 ቀናት ማለትም ከመጋቢት28- ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም 183 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ማጣታቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ የሞት ቁጥር ያስመዘገቡ ክልሎች፡
*አዲስ አበባ 98
*ኦሮሚያ 30
*አማራ 14
*ሐረሪ 14
*ሲዳማ 10 ናቸው፡፡
ኮቪድ 19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 208 ደርሷል፡፡
እስከ ትናንት እለትም 230 ሺህ 944 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ 171 ሺህ 980 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውንም ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል (አፍሪካ ሲ.ዲ.ሲ) በትናንትናው እልት ማስታወቁም ይታወሳል።
ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በኮቪድ 19 በከፍተኛ ደረጃ የተጠቁ ሀገራት መሆናቸውን ከማዕከሉ የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል።
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ4.3 ሚሊዮን መሻገሩን የገለጸው ማዕከሉ በወረርሽኙ የ115 ሺህ 418 ሰዎች ህይወት አልፏል ብሏል።