ባለፉት 3 ዓመታት ያለ ህጋዊ ሰነድ በሳዑዲ ይኖሩ የነበሩ ከ4 መቶ ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል
ከባለፈው መጋቢት ወዲህ ከ4 ሺ 4 መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ተመልሰዋል
ዜጎቹ ከግንቦት 2009 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 2012 ዓ/ም የተመለሱ ናቸው
ባለፉት 3 ዓመታት ያለ ህጋዊ ሰነድ በሳዑዲ ይኖሩ የነበሩ ከ4 መቶ ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያለህጋዊ ሰነድ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በመጋቢት 2009 ዓ/ም ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ከ400 ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስታወቀ፡፡
ዜጎቹ ከግንቦት 2009 ዓ/ም ጀምሮ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሃገሪቱ እስከተከሰተበት እስከ መጋቢት 2012 ዓ/ም የተመለሱ መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ወረርሽኙ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጀምሮ በመጀመሪያው ዙር በተደረገ የማስመለስ ስራ በሳዑዲ ይኖሩ የነበሩና ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ 3 ሺ 500 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
ሃገር ቤት ከገቡ በኋላ ከወረርሽኙ ነጻ መሆናቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በማቆያ እንዲቆዩና ደህንነታቸው ተጠብቆ በየመጡበት አካባቢ ተመልሰው ከዘመዶቻቸው ጋር መደበኛ ኑሯቸውን እንዲመሩ መደረጉንም ገልጿል።
በተመሳሳይ በተያዘው አዲሱ ዓመት መባቻ ጀምሮ በ2ኛው ዙር ለመመለስ ከታቀደው 2 ሺ ኢትዮጵያዊያን መካከልም እስከዛሬ ድረስ 964 ያህሉ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመለሱት መካከል አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት ሲሆኑ ከወረርሽኙ ነጻ እስኪሆኑ ድረስ በማቆያ እንዲያሳልፉና ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥ ወደ የመጡበት አካባቢ እንዲቀላቀሉ ተድርጓል።
ሆኖም ኢትዮጵያውያኑ አሁንም ተመልሰው በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በድጋሚ ያለህጋዊ ሰነድ ወደ ሳዑዲ ተጉዘዋል እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፡፡
በወረርሽኙ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በርካታ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ለከፍተኛ ችግሮች ተጋልጠው እንደሚገኙ ይታወቃልም ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
መንግስት ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ዜጎች ተገቢውን ክብር እንዲያገኙና አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው እንዲኖሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡
ለዚህ ከምንም ነገር በላይ የቀደመ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ እንዲመለሱ ለማድረግ በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በየጊዜው ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ በቅንጅት በሰራቸው ተግባራት አበረታቸ ውጤቶች ተገኘተዋል።
በመሆኑም ዜጎች መብታቸው ክብራቸው ተጠብቆ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚያደርገውን ትብብርና ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስቴሩ ገልጿል።