ከመጋቢት 22 አንስቶ በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ ህይወት አልፏል
ከመጋቢት 22 አንስቶ በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ ህይወት አልፏል
በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡
ታማሚዋ መጋቢት 19/2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22/2012 ዓ.ም የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡
ግለሰቧ መጋቢት 6/2012 ዓ.ም ከፈረንሳይ የተመለሱ የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደነበሩ የጤና ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በሰጠው መግለጫ ተካቷልል፡፡
ዛሬ መጋቢት 27 ህይወታቸው ያለፈው የ60 ዓመት በቫይረሱ መያዛቸው በተረጋገጠ እለት የተሰጠ መግለጫ
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባወጡት መግለጫ እንዳሉት ታማሚዋ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ ህክምና ሲደረግላቸው ነበር። ከቀናት በፊት ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል ተዛውረው ጥብቅ ክትትል ሲደረግላቸው የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል። በዚህም ሚኒስትሯ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በኮሮና ቫይረስ በተከሰተው የኢትዮጵያዊት ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጸዋል፡፡
“በኮቪድ19 ሕይወቷ ላለፈው ኢትዮጵያዊት ቤተሰብ እና ወዳጆች ከልቤ መጽናናትን እመኛለሁ፤ ነፍሷ ዘላለማዊ ረፍትን ታግኝ። ዜናውን የሰማችሁ ሁሉ እንድትረጋጉ እና የወጡትን መመሪያዎች በጥብቅ እንድትከተሉ አሳስባለሁ። የሚገጥመንን ሁኔታ በጋራ ለማስተናገድ በምንዘጋጅበት በዚህ ጊዜ፣ በእምነት ጸንተን ቫይረሱ በማኅበረሰባችን መካከል እንዳይሠራጭ በትጋት ልንሠራ ያስፈልጋል። አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ። እጆቻችሁን በሚገባ ታጠቡ። በምትችሉት መንገድ ሁሉ ለሌሎች ድጋፍ አድርጉ።” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪ አቅርቧል፡፡