በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዛሬው እለት ባደረገው ተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ የተያዙ ሁለት (2) ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ አንድ (21) ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ግለሰቦች የ38 ዓመት ወንደ እና የ35 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ ሁለቱም ግለሰቦች በተለያየ ቀናት ወደ ዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበራቸው ሲሆን የበሽታው ምልክት በማሳየታቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዘቸው ተረጋግጧል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ አስራ ሰባት (17) ታማሚዎች ሲኖሩ አንድ ታማሚ በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ሁለቱ ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው (ጃፓን) ተመልሰዋል፡፡
በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከተጠቀሰው በተጨማሪ አንድ ታማሚ ሙሉ በሙሉ ያገገመ ሲሆን ባጠቃላይ ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡ ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገብር ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡