ቤቲ ጂ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነች
ቤቲ ጂ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነች
በአፍሪካ የተለያዩ የሙዚቃ ሽልማቶችን ያሸነፈችው ቤቲ ጂ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆና ተሰይማለች፡፡
አርቲስቷ የUNHCR ደጋፊ በመሆን ከኮሚሽኑ ጋር በተለይም በኢትዮጵያ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች የተለያዩ ተግባራትን አከናውናለች፡፡
ቤቲ መመረጧን ተከትሎ “የዓለማችን ዋነኛ ተጋላጭ የሆኑትን ስደተኞችን ለማገልገል በመመረጤ ደስታና ክብር ተሰምቶኛል” ስትል ተናግራለች፡፡ “ኃላፊነቴንበሙሉ ትጋት ለመወጣት ዝግጁ ነኝም” ብላለች፡፡
በመድረክ መጠሪያዋ ቤቲ ጂ በመባል የምትታወቀው ብሩክታዊት ጌታሁን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ደረጃ እውቅናን እያተረፉ ከመጡ አርቲስቶች መካከል የምትጠቀስ ናት፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 በመላው አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (AFRIMA) በስድስት ዘርፎች ለእጩነት ቀርባ ሦስቱን አሸንፋለች፡፡
ከ2017 ጀምሮ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ስመጥር ደጋፊ የሆነችው ድምጻዊቷ 750,000 ያክል ስደተኞችን በምታስተናግደው ሀገሯ ኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የስደተኛ መጠለያ ካምፖችን እንደጎበኘች ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ከድምጻዊቷ ጋር በቅርበት መስራቱን እንደሚቀጥልም ነው የእስካሁን ተግባሯን ያደነቀው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡