ስፖርት
የለተሰንበት የ5 ሺ ሜትር ሪከርድ የዓለም ሪከርድ ሆኖ ተመዘገበ
ለተሰንበት ከ12 ዓመታት በፊት በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የርቀቱን ሪከርድ በ4 ሴኮንዶች ማሻሻሏ የሚታወስ ነው
የኡጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጊ የ10 ሺ ሜትር ሰዓትም የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል
አትሌት ለተሰንበት ግደይ በስፔን ቫሌንሺያ ያስመዘገበችው የ5ሺ ሜትር ሪከርድ የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዘገበ፡፡
ለተሰንበት በውድድሩ በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከ12 ዓመታት በፊት ተይዞ የነበረውን የርቀቱን ክብረ ወሰን በ4 ሴኮንዶች በማሻሻል 14፡06.62 መግባቷ የሚታወስ ነው፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ለተሰንበት በነገሰችበት ውድድር ነግሶ ቀነኒሳ በቀለ ለ15 ዓመታት ይዞት የነበረውን የ10 ሺ ሜትር ሪከርድበመስበር ያሸነፈው የኡጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጊ የርቀቱ ሰዓትም የዓለም ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ቼፕቴጊ የቀነኒሳን ሪከርድ በ6 ሴኮንዶች በማሻሻል ነበር 26፡11 የገባው፡፡
በቅርቡ በዚያው በቫሌንሺያ ከተማ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር የመጀመሪያ ተሳትፎዋን እንደምታደርግ ስትጠበቅ የነበረችው ለተሰንበት ትግራይ ክልል የነበረች መሆኗን ተከትሎ ከውድድሩ ውጭ መሆኗ አይዘነጋም፡፡