ልዩልዩ
በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሻምበል ፍቅረሥላሴ አረፉ
ሻምበል ፍቅረ ሥላሴ የአየር ኃይልን በመወከል ደርግን ከመሰረቱ ቀዳሚ አባላት መካከል አንዱ ነበሩ
ለ20 ዓመታት በእስር ላይ የቆዩት ሻምበል ፍቅረሥላሴ “እኛና አብዮቱ” የሚል መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል
በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በ 75 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አጠቃላይ የደርግ ዘመን የአቢዮት እንቅስቃሴና ውጤት ላይ ያተኮረ “እኛና አብዮቱ” የሚል መጽሐፍ ያሳተሙት ፍቅረ ስላሴ 20 ዓመታትን በእስር ቆይተዋል፡፡
ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ በእስር ቤት በነበረው የእስረኛ አያያዝ ምክንያት በተደጋጋሚ ይታመሙ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በጸና ታመው መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
ሻምበል ፍቅረ ሥላሴ የአየር ኃይልን በመወከል ደርግን ከመሰረቱ ቀዳሚ አባላት መካከል አንዱ ነበሩ፡፡