ስፖርት
አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረ-ወሰን አስመዘገበች
አትሌት ለተሰንበት ግደይ ርቀቱን 1:02:50 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው የአዲስ ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው
ለተሰንበት ግደይ በርቀቱ ከ1:04ና 1:03 ሰዓት በታች መግባት የቻለች የዓለማችን የመጀመሪያዋ ሴት መሆን ችላለች
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቫሌንሺያ የተካሄደውን የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር 1ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።
አትሌት ለተሰንበት ግደይ ርቀቱን 1:02:50 በሆነ ሰዓት በመግባት በርቀቱ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በእጇ ማስገባት ችላለች።
የሴቶች ግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ከዚህ ቀደም በኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕንጌቲች 1:04:02 በሆነ ሰዓት ተይዞ ቆይቷል።
አትሌት ለተሰንበት ግደይ በርቀቱ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን ከአንድ ደቂቃ በላይ በማሻሻል ነው በርቀቱ የአዲስ ክብረወን ባለቤት መሆን የቻለችው።
ለተሰንበት ግደይ በሴቶች ግምሽ ማራቶን ከ1:04 እና 1:03 ሰዓት በታች መግባት የቻለች የዓለማችን የመጀመሪያዋ ሴት ነች ብሏል አትሌቲክስ ዊክሊ።
የ23 ዓመቷ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቶኮዮ ኦሎምፒክ ላይ በ10000 ሜትር ተወዳድራ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ እንደነበረች ይታወሳል።
በቫሌንሺያ ግምሽ ማራቶን በወንዶች በተካሄደው ውድድር ኬንያዊው አትሌት አቤል ኪፕቹማ 58:03 በሆነ ሰዓት በመግባ ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል።