ሲፋን ሃሰን የአውሮፓ የዓመቱ አትሌት ተብላ ተመረጠች
የ28 ዓመቷ አትሌት በኦሎምፒክ ውድድሩ ማጠናቀቂያ የደች (ሆላንድ) ሰንደቅ ዓላማ አውለብላቢ ነበረች
ሲፋን የቶኪዮ ኦሎምፒክ የ10 እና የ5 ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል
የአውሮፓ አትሌቲክ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን ሆላንዳዊ አትሌት ሲፈን ሃሰንን የዓመቱ ምርጥ የአውሮፓ አትሌት አድርጎ መረጠ፡፡
የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ሲፋን የዓመቱ ምርጥ ሴት የአውሮፓ አትሌት ሆና የተመረጠችው ትናንት ቅዳሜ ምሽት በስዊዘርላንድ ሎዛን በተካሄደ የ‘ጎልደን ትራክስ’ የእውቅና ስነ ስርዓት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ የፓሪስ ማራቶንን አሸነፉ
ሲፋን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ሁለት የወርቅ እና አንድ የነሃስ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች፡፡ የወርቅ ሜዳሊያዎቹ በ5 ሺ እና 10 ሺ ሜትር፤ የነሃስ ሜዳሊያው ደግሞ በ1 ሺ 500 ሜትር የተገኘ ነው፡፡
የ28 ዓመቷ አትሌት በኦሎምፒክ ውድድሩ ማጠናቀቂያ የደች (ሆላንድ) ሰንደቅ ዓላማ አውለብላቢ ነበረች፡፡
በሽልማቱ መደሰቷን የገለጸችው ሲፋን ሸላሚዎቹን፣ አሰልጣኞቿን፣ ቤተሰቦቿን እና አድናቂዎቿን አመስግናለች፡፡
ትዕግስት ገዛኸኝ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የፓራሊምፒክ ወርቅ አስገኘች
ሲፋን በ2019 በኳታር ዶሃ በተካሄደ የ10 ሺ ሜትር ውድድር አሸናፊም ነበረች፡፡ ለታዋቂው አክተር ጂን ክላውዴ ቫንዳም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በብራሰልስ ቤልጂዬም በተካሄደ ውድድርም ከምንጊዜም ፈጣን ሰዓቶች መካከል 5ኛውን አስመዝግባለች፡፡