ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጸሃይ ገመቹ በኮፐንሀገን ግማሽ ማራቶን አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዘገበች
የኮፐንሀገን ግማሽ ማራቶን 20ሺ ገደማ ተሳታፊወች ታድመውታል ተብሏል
በወንዶች ግማሽ ማራቶን ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 1ኛ ደረጃ በመውጣት አሸንፏል
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጸሃይ ገመቹ በኮፐንሀገን ግማሽ ማራቶን አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዘገበች፡፡
የ22 ዓመቷ አትሌት ጸሃይ የገባችበት ሰዓት 1:05:08 ሲሆን ይህም ቀደም ሲል በኦሎምፒክ የሁለት ወርቅ አሸናፊዋና ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሃሰን እንደፈረንጆቹ በ2018 ተይዞ ነበረውን ክብር ወሰን በሰባት ሴኮንዶች ያሻሻለ ነው ተብለዋል፡፡
በውድድሩ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሃዊ ፈይሳ በ1:05:41 ሁለተኛ ስትወጣ ኬንያዊቷ አትሌት ቪቭያን ኪፕላጋት በ1:06:07 ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች፡፡
ሌላው ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የወንዶች ግማሽ ማራቶን አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ በ59:10 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ሲያሸንፍ ኬንያዊው አትሌት ኬንት ቤንጁ 59፡12 በሆነ ሰዓት 2ኛ እንዲሁም ሌላኛው ኬንያዊ አትሌት ዳንኤል ማትየኮ 59፡25 በሆነ ሰዓት 3ኛ ሆነው አጠናቋል፡፡
ለአንድ ዓመት ተኩል ተቋርጦ ነበረው የሲፒኤች ግማሽ ማራቶን ውድድር ወደ ኮፐንሃገን ጎዳናዎች የተመለሰ ሲሆን ከመላው ዓለም የመጡ ወደ 20,000 ገደማ ተሳታፊዎች አየተስተናገዱበት ነው፡፡
“21.0975 ኪሎሜትር የሸፈነው የዓለማችን ፈጣኑ የኮፐንሀገን ግማሽ ማራቶን” የበርካቶች ቀልብ ስቦ እና ተወዶ እንዳለፈ የውድድሩ አዘጋጆች ስፓርታ አትሌቲክ እና ሎብ ገልጸዋል፡፡