በበርሊን ማራቶን በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን ከ1ኛ ስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል
ተጠባቂ የበርሊን ማራቶን በዛሬው እለት በጀርመኗ በሪሊን ከተማ ተካሂዷል።
በውድድሩንም ኢትዮጵያዊው አትሌት ጉዮ አዶላ 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል።
በውድድሩ ከፍተኛ አሸናፊነት ግምት ተሰጥቶት የነበረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ያፀናቀቀ ሲሆን፤ ኬንያዊው አትሌት ቤትዌል ዬጎን 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በበርሊን ማራቶን በሶቶች በተካሄደው ውድድርም ኢትዮጵያውያን ከ1ኛ ስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት በበላይነት አጠናቀዋል
በዚህም መሰረት አትሌት ጎይቶም ገ/ስላሴ 1ኛ፣ አትሌት ህይወት ገኪዳን 2ኛ እንዲሁም አትሌት ሔለን ቶላ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
አሸናፊዋ አትሌት አትሌት ጎይቶም ገ/ስላሴ ርቀቱን 2 ሰዓት 20 ደቂቃ ከ09 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ 1ኛ ደረጃን መያዝ ችላች።
አትሌት ህይወት ገኪዳን 2 ሰዓት 21 ደቂቃ 23 ሰከንድ በመግባ 2ኛ እንዲሁም አትሌት ሔለን ቶላ 2 ሰዓት 23 ደቂቃ 05 ሰከንድ በመግባ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።