ኢትዮጵያ የሶማሊያ መንግስት የሚያወጣቸውን ጠብ አጫሪ መግለጫዎች እየተከታተልኩ ነው አለች
በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያላንድ የወደብ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ነው
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ "ለወንድም የሶማሊያ ህዝብ" ሰላም እና መረጋጋት ለሶስት አስርት አመታት በላይ ዋጋ ከፍላለች ብሏል
ኢትዮጵያ የሶማሊያ መንግስት የሚያወጣቸውን ጠብ አጫሪ መግለጫዎች እየተከታተልኩ ነው አለች።
የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያወጣቸውን ተደጋጋሚ ጠብ አጫሪ መግለጫዎች እየተከታተላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፊስቡክ ገጹ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ሶማሊያ የራሷ ሉአላዊ ግዛት አካል አድርጋ የምታያት ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ የወደብ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ነው።
ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉአላዊነትና አለማቀፉን ህግ ጥሳለች - ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ
ስለባህር በር የሚደረጉ ንግግሮች ግራ አጋቢ እንደሆኑበት የኤርትራ መንግስት ገለጸ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ የሶማሊያ መንግስት ከሚያቀርበው "መሰረተቢስ ክስ" በተቃራኒ "ለወንድም የሶማሊያ ህዝብ" ሰላም እና መረጋጋት ከሶስት አስርት አመታት በላይ ዋጋ ከፍላለች ብሏል።
ኢትዮጵያ በሶማሊያ የመንግስት ባለስልጣናት በሚሰጡ መሰረተቢስ እና ኃላፊነት በማይሰማቸው መግለጫዎች ኢትዮጵያ ሶማሊያን በመገንባት ያላትን ሚና ለመካድ መመከራቸው ቅር እንዳሰኛት ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሶማሊያ ጠብ አጫሪ መግለጫዎችን ብትሰጥም፣ ኢትዮጵያ ለሁለቱ ህዝቦች ጥቅም ስትል ንግግርን መርጣለች ብሏል ሚኒስቴሩ።
ግጭቶች እየተካሄዱ ባለበት የአፍሪካ ቀንድ ያለው የጦር መሳሪያ ዝውውር ያሳስበኛል ያለችው ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ወንጀሎችን ለማስቆም ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገልጻለች።
ሶማሊያ የወደብ ስምምነቱ አለምአቀፍ ህግን እና ሉአላዊነቷን እንደሚጥስ በመግለጽ ነበር የተቃወመችው።
በስምምነቱ "የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም"- የኢትዮጵያ መንግስት
በስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገር እውቅና እንድትሰጥ በምላሹ ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ 20 ኪሎሜትር የሚረዝም የባህር ጠረፍ ለ50 አመታት በሚቆይ የሊዝ ኪራይ ለንግድ እና ለባህር ኃይል ሰፈር እንድትጠቀም ያስችላል ተብሎ ነበር።
ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር በማባረር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጨረሶ እንዲበላሽ አድርጋለች።
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀመድ ኢትዮጵያ ስምምነቱን ካልሰረዘች ንግግር እንደማያደርጉ ሲናገሩ ተደምጠውም ነበር።
ነገርግን በቅርቡ ቱርክ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማግኘቷን እና በድጋሚ ተገናኝተው ለመምከር መስማማታቸውን መግለጿ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት የተፈራረመችው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀይ ባህር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ መሆኑን እና የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገራትም ይህን እንዲያስቡበት ከገለጹ በኋላ ነበር።