የፕሮጀክቱ ገንቢ ሳሊኒ፤ የሕዳሴ ግድብ “በርካታ ጠላቶች” አሉት ብለዋል
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በ 2017 እንደሚጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅክፍሌ ሆሮ (ኢ/ር) አስታወቁ፡፡
ዋና ስራ አስኪያጁ ፕሮጀክቱ ከሶስት ዓመታት በኋላ ተጠናቆ የሚጠበቅበትን 5ሺ 150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያላት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም 4 ሺ ሜጋ ዋት ግድ ሲጠናቀቅ ግን ይህ ቁጥር ከእጥፍ በላይ በሆነ ቀን እንደሚጨምር ኢ/ር ክፍሌ አስታውቀዋል፡፡
ግድቡ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ሲጠናቀቅም የሀገሪቱን 40 በመቶ የሃይል አቅርቦት እንደሚሸፍንም ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
ኢ/ር ክፍሌ በግድቡ ግንባታ ላይ መዘግየት እንደነበረ ያነሱ ሲሆን ፤ የመጀመሪያው ተርባይን በአራት ዓመት ውስጥ ስራ ይጀምራል የሚል ዕቅድ ነበረ ብለዋል፡፡ ይሁንና ፕሮጀክቱ ሲጀመር መንግስት ኮንትራቱን ለሁለት ከፍሎ በሀገር ውስጥ እንዲገነባ በማድረጉ የዕቅድና የቴክኒካል ችግር ነበረ ተብሏል፡፡ መንግስት በወቅቱ የግድቡን ውስብስ የነበረውን ስራ ለሜቴክ መስጠቱ፤ አሰጣጡ ስትራቴጂያዊ እንዳልነበረ ያመለክታል ብለዋል፡፡
የሕዳሴ ግድብ ማለቅ ያለበት በአራት ዓመታት ውስጥ ቢሆንም ባልተጠና ውሳኔ መሰረት እንደዘገየ መንግስት በተደጋጋሚ ገልጿል፡፡ ይሁንና ግድቡ በፈረንጆቹ ታህሳስ 2024 ወይንም 2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና ይጠናቀቃል፤ ተርባይኖቹ ተራ በተራ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል፡፡
ባለፈው ዓመት የተያዘው ውኃ ከታቀደው በታች ነው?
ባለፈው ዓመት ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት ሲከናወን ግብፅ፤ ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር የያዘችው ውኃ ካቀደችው ያነሰ ነው ብላ የነበረ ቢሆንም ኢ/ር ክፍሌ ደግሞ ውኃ መያዝ ደረጃ በደረጃ ነው የሚከናወነው መሆኑን አንስተዋል፡፡
የውኃ መያዝን በተመለከተ አንደኛ፣ሁለተኛ የተባለው ኃይል ለማመንጨት እንደሆነ የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ በወቅቱ የተያዘው ይህንን ኃይል ለማመንጨት በቂ ነውም ብለዋል፡፡ የሕዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባዮኖች የመጨረሻው ተርባይን ስራ የሚጀምረው በ 2017 ዓ.ም አጋማሽ አካባቢ እንደሆነ ኢ/ር ክፍሌ ገልጸዋል፡፡
የፕሮጀክቱን ግንባታ የሚያከናውነው የጣሊኑ ሳሊኒ ኢምፕሪጂሎ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ “ይህ ፕሮጀክት (ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት) በርካታ ጠላቶች እንዳሉት ገልጸው፤ የዓባይ ውኃ ለኢትዮጵያ ነጭ ጋዝ ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡