ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዛሬው እለት በ375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ጀምሯል
ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ ትልቅ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በዛሬው እለት ኃይል ማመንጨት ጀመረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ግድቡ እየተገነባ በሚገኝበት ጉባ ተገኝተው የግድቡን አንድ ተርባይን ሃይል የማመንጨት ስራ በይፋ አስጀምሯል።
በዚህም ግድቡ ካሉት ተርባይኖች ውስጥ አንዱ የሆነው እና ዩኒት 10 የሚል መጠሪያ ያለው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ጀምራል።
ከ10 ዓመት በፊት በአራት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተጀመረው ግድብ ባለፈው ነሐሴ ወር ኃይል ማመንጨት እንደሚጀመር የወቅቱ የውሃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ገልጸው ነበር፡፡
ሚኒስትሩ የግድቡን 10ኛ አመት አስመልክተው ባሰሙት ንግግር ሁለቱ ተርባይኖች ግንባታቸው ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል ብለው ነበር፡፡
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የመረሰት ድንጋይ ካስቀመጠች አንድ አመት በኋላ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግብጽና ሱደን በግድቡ ላይ ስጋት እንዳላቸው ጥያቄ አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ በግድቡ አስተዳደር ጉዳይ የሶስትዮች ንግግር እና ድርድር ከመጀሩ ቆይተዋል፤ ነገርግን እስካን ከስምምነት አልደረሱም፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡን እየገነባ ያለው ለልማት አላማ ብቻ መሆኑን እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የጎላ ተጽእኖ እንደማያደርስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ግብጽና ሱዳን ግን በግድቡ ዙሪያ የየራሳቸው አቋም አላቸው፡፡
በተለይም ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረመ ስምምነትን ጭምር በመጥቀስ፤ ታሪካዊ የሆነ የውሃ ድርሻዋ ላይ ተጽእኖ እንሚያሳድር እና ግድቡ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድርባት ትገልጻለች፡፡
በ2013 ዓ.ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ከፈረስ በኋላ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አመቻችነት እንዲካሄድ ተስማምተዋል፡፡
ድርድርሩ ወደ አፍሪካ ህብረት የመጣው ኢትዮጵያ፤ ድርድሩ ሳይጀመር የታዛቢነት ሚና የነበራቸው አሜሪካና የአለም ባንክ ሚናቸውን ወደ አደራዳሪነትና ወደ የስምምነት ሰነድ አርቃቂነት ከፍ በማድረጋቸው እና ኢትዮጵያም ይህን አልቀበልም በማለቷ ነው።
ኢትዮጵያ የግድቡ ጉዳይ የልማት ጉዳይ ነው ብትልም ፤ግብጽና ሱዳን የግድቡን ጉዳይ የጸጥታ ጉዳይ ነው በማለት ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት በማቅረብ ም/ቤቱ ወይይት አድርጎበት ያውቃል።