በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መብት እንዲበር ለመምከር ልኡክ መላኩን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ
በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መብት እንዲበር ለመምከር ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከሌሎች ከሚመለከታቸው ኤጄንሲዎች የተውጣጣ ልኡክ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መሄዱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ልኡክ ቡድን ከሳኡዲ ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መብት የሚከበርበትንና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሰላም የሚመለሱበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡
በኢትዮጵያና በሳኡዲ ባለስልጣናት መካከል የሚደረገው ውይይት ለመመለስ ፍቃደኛ የሆኑ ስደተኞችን በመመለስ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ይገመግማል ብሏል መግለጫው፡፡
በኢትዮጵያ የሳኡሲ አረቢያ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ ወደ ሳኡዲ የመግባት ሙከራ ወቅያኖስ ውስጥ ከመስጠምና የሀዉዚ ታጣቂዎች ጥቃት ሰለባ መሆን ጨምሮ በርካታ አደጋዎች እንዳሉት ገልጿል፡፡
የሳኡዲ አረቢያ ድንበር ሰፊ በመሆኑ ስደተኞች ድንበር አልፈው መግባት አይሳካላቸውም፤ የስደተኖቹንም ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብሏል፡፡
የሳኡዲ መንግስት የድንበር የጸጥታ ህግን በሚጥሱ ላይ ቅጣት እንደሚጥልና ከድንር አካባቢ ሰዎች የሚያዘዋዉሩትንም እንደሚከለክል አስታውቋል፡፡