ልዩልዩ
ፍርድ ቤቶች ለ15 ቀናት በከፊል ዝግ ሊሆኑ ነው
“…አስቸኳይ እርምጃ የሚፈልጉ ጉዳዮች ግን እንዲታዩ ይደረጋል”- የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መአዛ
በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ፍርድ ቤቶች ለ15 ቀናት በከፊል ዝግ እንዲሆኑ ተወሰነ
በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ፍርድ ቤቶች ለ15 ቀናት በከፊል ዝግ እንዲሆኑ ተወሰነ
ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ ፍርድቤቶች ከመጋቢት 10-24 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት አስታውቋል፡፡
ፍርድቤቱ ባወጣው መግለጫ “ከፍርድ ቤቶች የዳኝነት አሰጣጥ የስራ ባህሪይ አንጻር ወረርሽኙ በፍርድቤቱ ማህበረሰብና ተገልጋዮች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል” ብሏል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መአዛ አሸናፊ በትዊተር ገጻቸው “የሀሙስና የአርብ ዳኞች ጉዳዮችን ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ይቀጥራሉ፤ ፍርድቤቶች አዲስ ጉዳዮችን አይቀበሉም፤ አስቸኳይ እርምጃ የሚፈልጉ ጉዳዮች ግን እንዲታዩ ይደረጋል” ብለዋል፡፡
እንደ መግለጫው ከሆነ ዳኞች ከመጋቢት 10-24፤ 2012 ተቀጥረ ው የነበሩ ደንበኞችን እንደጉዳያቸው እየታየ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስት የኮሮና ቫይረስ ከገባ ከባለፈው አርብ ጀምሮ እስካሁን 6 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ መንግስት ስርጭቱን ለመግታት በማሰብ ትምህርት ቤቶች ለ15 ቀናት ዝግ እንዲሆኑና ስብሰባዎችም እንዳይካሄዱ መንግስት አሳስቧል፡፡