ኢትዮጵያ በኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር ቀዳሚ ስትሆን ሱዳን ደግሞ በሟቾች ቁጥር ትበልጣለች
ኢትዮጵያ በኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር ቀዳሚ ስትሆን ሱዳን ደግሞ በሟቾች ቁጥር ትበልጣለች
ኢትዮጵያ በኮሮና ተጠቂ ሰዎች ቁጥር ከ14 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ መሆኗን የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማእከል መረጃ አመልክቷል፡፡
ማእከሉ ዛሬ ባወጣው መረጃ ኢትዮጵያ እስካሁን በ32722 ሰዎች በኮሮና የተጠቁባት ሲሆን 572 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት መካከል እስካሁን 12938 ሰዎች ማገገም ችለዋል፡፡ ሱዳን በአንፃሩ በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን ባጡ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ ነች፡፡
እንደማእከሉ መረጃ በሱዳን እስካሁን 805 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ኬንያና ሱዳን ከኢትዮጵያ ቀጥሎ 2ኛና 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡
ዓለምአቀፍ ወረርሽኝ የሆነው ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ከተረጋገጠበት መጋቢት 4፣ 2012 ዓ.ም በኋላ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል መንግስት የየብስ ድንበርን ለሰው ዝውውርን ከመዝጋት እስከበረራ ማቋረጥ የደረሰ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል፡፡ ትምህርትቤቶች እስካሁን ዝግ እንደሆኑ ናቸው፡፡
ስርጭቱን ለመግታት ተጨማሪ ርምጃዎች ያስፈልጉኛል ያለው መንግስት እስከ ነሀሴ ወር ድረስ የሚቆይ የአምስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፡፡ አዋጁ ማስክ( የፊት ጭምብል) ማድረግን፣ከአራት ሰዎች በላይ የሚደረግ ስብሰባን መከልከልንና የተለያዩ የትራንስፖርት መመሪያዎች የያዘ ነው፤እየተተገበረም ይገኛል፡፡