ኢትዮጵያ በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እየተሳተፈች ነው
ቡድኑ እንደ ሃገር እየተካሄዱ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮችን ለማሳየት በሚያስችል የበይነ መረብ ኤግዚቢሽን ይሳተፋል ተብሏል
ኢትዮጵያን በመወከል በአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕ/ር ፍቃዱ በየነ የሚመራ ቡድን በጉባዔው እየተሳተፈ ይገኛል
ኢትዮጵያ ዛሬ በስኮትላንድ ግላስኮው በተጀመረው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ26) ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
ኢትዮጵያን በመወከል በአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕ/ር ፍቃዱ በየነ የሚመራ ቡድን በጉባዔው እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ በ10 ሚሊየን ሰዎችን ሊያፈናቅል ይችላል- የዓለም ባንክ
ከኮሚሽኑ እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ቡድኑ ከጉባዔው ጎን ለጎን በሚካሄዱ የጋርዮሽ ድርድሮችና ስምምነቶች ይሳተፋል፡፡
የኢትዮጵያን ጥቅሞች ሊያስጠብቁ የሚችሉ የተለያዩ የጎንዮሽና የሁለትዮሽ መድረኮችንም ያዘጋጃል፡፡ እንደ ሃገር እየተካሄዱ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮችን ለማሳየት በሚያስችል የበይነ መረብ ኤግዚቢሽንም ይሳተፋል።
ቡድኑ በተለይም በተሻሻለውና በፈቃደኛነት ላይ የተመሠረተውን የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድን በተመለከተ እንዲሁም የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ስላስገኛቸው ጠቀሜታዎች ለባለድርሻዎችና ለልማት አጋሮች ተሞክሮውን እንደሚያቀርብም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በብሪታኒ አዘጋጅነት በግላስኮው መካሄድ በጀመረው የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ የተለያዩ ሃገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዓለምን የሙቀት መጠን ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ እንዳያልፍ ለማድረግ የገባነውን ቃል እንጠብቅ ብለዋል፡፡
ይህ ትልቅ ስራን እንደሚጠይቅ እና እንደ ፈረንጆቹ በ2030 የዓለምን የካርበን ልቀት በ45 በመቶ ለመቀነስ የሚያስችሉ ጠንካራ እርምጃዎች እንደሚስፈልጉ ም ገልጸዋል፡፡
ዩኤኢ 28ኛውን የተመድ የአየር ንብረት ጉባዔ በአቡዳቢ ለማዘጋጀት ጠየቀች
የዓለምን የሙቀት መጠን ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ እንዳያልፍ ማድረግ ማለት ልቀቱን እስከ 2030 በግማሽ ለመቀነስና በ2050 ደግሞ ዜሮ ለማድረግ የሚያስችል ነው እንደ ዘርፉ ባለሙያዎች ገለጻ፡፡
ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ በጣሊያን ሮም ተሰብስበው የነበሩ የቡድን 20 አባል ሃገራትም ስለ አየር ንብረት ለውጥና ስለ ካርበን ልቀት አሳሳቢነት ተወያይተዋል፡፡
ሆኖም ምን መወሰድ ስላለበት እርምጃ ሙሉ ስምምነት ላይ አልደረሱም፡፡
መሪዎች ንግግር እያደረጉበት የሚገኘው ዓለም አቀፉ ጉባዔ እ.አ.አ. በ2050 የተጣራ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን ዜሮ ማድረግ (Zero-Net Emission 2050) በሚል መሪ ሀሳብ ነው ዛሬ መካሄድ የጀመረው፡፡ እስከ ነገ ወዲያ ረቡዕ ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስም ይቆያል፡፡