በኢትዮጵያ ከግማሽ የሚበልጡ የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ በጥናት ተረጋገጠ
የትምህርት ስርዓቱ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራ እንደሚገባም በጥናቱ ተጠቁሟል
በጥናቱ 68 በመቶ የ2ኛ ክፍል ተማሪዎችና 51 በመቶ 3ኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ተይቷል
በኢትዮጵያ ከግማሽ የሚበልጡ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ አዲስ የተሰራ ጥናት አመላክቷል።
ራይዝ ኢትዮጵያዊ የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም በአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የጥናት ውጤት በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።
ራይዝ ኢትዮጵያዊ በሰራው ጥናተም 68 በመቶ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51 በመቶ የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ማረጋገጡን አስታውቋል።
- ተመድ በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 93 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው አለ
- ከ12 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተናን እንዳልወሰዱ ተገለጸ
በኢትዮጽያ በ168 የተለያዩ የአንደኛ ደረጃ ትመህህርት ቤቶች በሚገኙ በ9 ሽህ ተማሪዎች በተጠናዉ ጥናት መሰረት 68 በመቶ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51 በመቶ የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ተገልጿል።
በተጨማሪም በቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ለይ እና ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብና መፃፍ፣ ሂሳብ ማስላት፣ የተረጋጋ ስነ-ልቦና እና መልካም ማህበራዊ መስተጋብርን የመሰሉ መሰረታዊ ክሎት እንዲኖራቸው መሰራት አለበት ተብሏል።
የተማሪዎችን የትምህርት ዉጤት ለማሻሻል የትምህርት ስርዓቱ የተናበበና የተቀናጀ ትግበራ እንደሚያስፈልገው በጥናቱ ላይ ተመልክቷል።
በጥናቱ ላይ የትምህርት ስርዓቱ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራ እንደሚገባ መጠቆሙን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል።
በዓለም ባንክ ይደገፋል የተባለው ራይዝ ኢትዮጵያ በትምህርት ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋቋመ ድርጅት ነው።