የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ63 ተጠርጣሪዎችን ክስ አቋረጠ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ63 ተጠርጣሪዎችን ክስ አቋረጠ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና የህግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ የመንግስትና የግል ባንኮች ላይ የተፈጸሙ ከባድ የሙስና ወንጀሎችና በሰብኣዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ አካላትን ለህግ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም ተቋሙ ለሀገራዊ አንድነት እና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል የ63 ተጠርጣሪዎች ክስ መቋረጡን አስመልክቶ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ለሚድያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት በተቋሙ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋ እንደገለጹት በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ 63 ተጠርጣሪዎች ለሀገራዊ አንድነት እና ለለዉጡ የሚኖረውን ፋይዳ ከግምት ዉስጥ በማሰገባት እንዲሁም ለህዝብና ለመንግስት ጥቅም ሲባል ተጠርጣሪዎቹ በወንጀሎች ዉሰጥ እንዳሉ የተረጋገጠ ቢሆንም ካሰከተሉት ጉዳት አንጻር ጉልህ ሚና የሌላቸው መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረውና ምርመራ ተጣርቶባቸው፣ ማስረጃ የተሰበሰበባቸው እና ክስ ተመስርቶባቸው በሙስና ወንጀል ከሜቴክ ጋር በተያያዘ፣ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር የተጠርጠሩ ነገር ግን የመሪነት ሚና የሌላቸው፣ ከሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የከፍተኛ አመራሮች ግድያ ጋር ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየታየ ያሉ፣ ከሲዳማ፣ ቤንሻንጉል እና የሶማሌ ክልል ግጭቶች ጋር በተያያዘም የተጠረጠሩ ጭምር ክከሳቸው ከተቋረጠው መካከል እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
በተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በበኩላቸው በአንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ያለዉ ግጭት፣ ሁከትና ብጥብጥ መንግስት ተረጋግቶ ለዉጡን እንዳይመራ እንቅፋት እየፈጠረ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን ይሄም ለሰው ህይወት መጥፋት፣ ለህዝብና መንግስት ሀብትና ንብረት መውደም፣ ለበርካቶች ከአካባቢያቸው መፈናቀል ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡
ስለሆነም በዚህ አስከፊ የወንጀል ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላትን ለይቶ ለሕግ በማቅረቡ በኩል ግጭቶት በተከሰተባቸው አካባቢያዎች በሙሉ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ በጋራ ተቀናጅተው ምርመራ በማጣራት ተጠርጣሪዎችን ለህግ ለማቅረብ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም አጠቃላይ ከሚፈለጉት 3,606 ተጠርጣሪዎች መካከል 1,682 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የገለጹ ሲሆን ሌሎች በወንጀሉ ላይ በቀጥታ ተሳትፎ ያላቸው ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ሥራ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል የተለያዩ ፍላጎታቸውን ለማሳካት በሙስና፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የብሔር እና የሃይማኖት እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግጭት በማነሳሳት ወንጀል ዉስጥ የተሳተፉ በመንግስትም ሆነ ከመንግስት መዋቅር ውጭ ያሉ ግለሰቦች መንግስት የህግ የበላይነትን እንደማያስከብር ለማስመሰልና የወንጀል ድርጊቶቻቸዉ እንዳይጋለጡ በማሰብ፤ በሕዝብ ዉስጥ ተደብቀው እንደሚገኙ አብራርተዋል:: ይሁን እንጂ በየደረጃ ካለዉ የመንግሰት የፖለቲካ አመራሮች ጋር በተደረገው ግልጽ ውይይትና በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች በሙሉ ህጉ በሚፈቅደው አግባብ ያለቅደመ ሁኔታ እንዲያዙ እየተደረገም ይገኛል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ከዚህ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሆነ በማንኛውም አግባብ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ብሔርን፣ ሃይማኖትን፣ ማንነትን መሰረት በማድረግ ግጭትና ብጥብጥ ለመፈጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ለሀገር ደህንነት ሲባል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑም ጠቁመዋል፡፡
በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክሳቸዉ እንዲቋረጥ የተደረጉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር፡-
1. ሌ/ኮ/ል ቢኒያም ተወልደ
2. ሌ/ኮ/ል ሰላይ ይሁን
3. ሌ/ኮ/ል ጸጋዬ አንሙት
4. ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ
5. ኮ/ል ግርማ ማንዘርጊያ
6. ኮ/ል ዙፋን በርሄ
7. ኮ/ል አሰመረት ኪዳኔ
8. ሻ/ል ይኩኖአምላክ ተሰፋዬ
9. አቶ አለም ፍጹም
10. አቶ ሰለሞን አብርሃ
11. አቶ ሰመረ ኃይለ
12. አቶ ክፍላይ ንጉሴ
13. ሌ/ኮ/ል መንግስቱ ከበደ
14. ሌ/ኮ/ል እሥራኤል አሰፋው
15. ሌ/ኮ/ል ከተማ ከበደ
16. ሌ/ኮ/ል ለተብርሃን ደሞዝ
17. አቶ ኡስማን ከበደ
18. ሌ/ኮ/ል ዋቅቶላ አዲሱ
19. ሌ/ኮ/ል ታቦር ኢዶሳ
20. ሻ/ል ዩሐንስ ትኬሳ
21. ወ/ሮ ወላንሳ ገ/ኢየሱስ
22. ሻ/ቃ ረመዳን ለጋስ
23. አቶ ሙሉጌታ ሰይድ
24. አቶ ዋሴዕ ሳድቅ
25. አቶ ሲሳይ ደበሌ
26. አቶ አክሊሉ ግርማይ
27. ወ/ሮ ራህማ መሀመድ
28. ወ/ሮ ዘምዘም ሀሰን
29. ኮ/ር ፋሩቅ በድሪ
30. አቶ አሳጥረው ከበደ
31. አቶ ሲሳይ አልታሰብ
32. አቶ አበበ ፋንታ
33. አቶ አሰቻለዉ ወርቁ
34. አቶ ተሾመ መለሰ
35. አቶ አለምነህ ሙሉ
36. አቶ ከድር ሰይድ
37. አቶ አዲስ አማረ
38. አቶ አማረ ብሌ
39. አቶ ክርስቲያን ታደለ
40. አቶ በለጠ ካሳ
41. አቶ ሚፍታህ ሸምሱ
42. ዶ/ር ማቴ ማንገሻ
43. አቶ ታሪኩ ለማ
44. አቶ ጌታሁን ዳጉይ
45. አቶ በላይ በልጉዳ
46. ሪ/ፓ/ር አመሉ ጣሚሶ
47. አቶ ተፈራ ቄንፈቶ
48. ረዳት ፕሮፈሰር ተሰማ ኤልያስ
49. አቶ አማኑኤል በላይነህ
50. አቶ አዲሱ ቃሚሶ
51. ሱ/ኢ/ አሰገል ወ/ጊዩርጊስ
52. ሱ/ኢ/ አሰፋ ኪዳኔ
53. ሱ/ኢ/ ገ/እግዚአብኤር ገ/ሃዋርያት
54. አቶ ግርማ አቡ
55. አቶ አብዱልሙኒየር አብዱልጀሊስ
56. አቶ ቶፊቅ አብዱልቃድር
57. አቶ ከማል መሃመድ
58. ኮ/ር ኡስማን አህመድ
59. ኮ/ር ኤዶሳ ጎሽ
60. አቶ ባበከር ከሊፋ
61. ዋ/ሳ/ እቴነሽ አርፋይኔ
62. አቶ ኤርሚያስ አመልጋ
63. አቶ ሙሉጌታ ሰይድ