ከኬንያ፣ ሱዳንና ጅቡቲ በተጨማሪ ለታንዛኒያ ሀይል መሸጥ ሊጀመር እንደሚችልም ተገልጿል
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እንዳለው በ2016 በጀት ዓመት ከኤሌክትሪክ ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅጃለሁ ብሏል።
ከሚሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 20 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ ደንበኞች ቀሪውን ደግሞ ከጎረቤት ሀገራት እንደሚሰበሰብም ተገልጿል።
እንደ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ሀይል እየተላከ ሲሆን ከታንዛኒያ ጋር የሀይል ሽያጭ ለመጀመር ውይይት እየተካሄደ ነው።
ይህ የሁለትዮሽ ስምምነት ከተጠናቀቀ በዚሁ 2016 ሀይል ወደ ታንዛኒያ መላክ እና መሸጥ ይጀምራል።