ከኒዩክሌር ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ ሀገራት
በ33 ሀገራት የሚገኙ 440 የኒዩክሌር ማብለያዎች የኤሌክትሪክ ሃይል እያመረቱ ይገኛሉ
ከኒዩክሌር ከፍተኛ ኤሌክትሪክ በማመንጨት አሜሪካ ቀዳሚውን ደረጃ ትይዛለች
ከኒዩክሌር የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት ጥረት በፈረንጆቹ 1950ዎቹ ተጀምሮ በየጊዜው እድገት ሲያሳይ ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅትም በ33 ሀገራት 440 የኒዩክሌር ሃይል ማመንጫዎች እንዳሉ የአለማቀፉ የኢነርጂ ተቋም መረጃ ያሳያል።
ቻይና፣ ህንድ እና ሩሲያን ጨምሮ በ15 ሀገራት 60 የኒዩክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።
ከኒዩክሌር የሚገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል ከአለማቀፉ አጠቃላይ የሃይል ምርት 10 በመቶውን የሚሸፍን ሲሆን፥ የጽሃይ እና ንፋስ ሃይል የሚሰጡትን ሃይል ድምር ይበልጣል።
የታዳሽ ሃይል ማመንጫዎች መስፋፋት ከኒዩክሌር የሚገኘውን ሃይል ጠቅላላ ድርሻ እየቀነሰ እንዲሄድ ቢያደርገውም አሁንም ድረስ የበርካታ ሀገራትን የሃይል ፍላጎት ለማሟላት እየዋለ ነው።
ከኒዩክሌር ከፍተኛ ኤሌክትሪክ በማመንጨት አሜሪካ ቀዳሚውን ደረጃ ትይዛለች።
ከጠቅላላ የኤሌክትሪክ ምርታቸው የኒዩክሌር ሃይል ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ ግን ፈረንሳይ (62 በመቶ)፣ ስሎቬኒያ (59 በመቶ) እንዲሁም ዩክሬን (55 በመቶ) ከፊት ይቀመጣሉ።
ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ ጥያቄ የሚነሳበትን ኒዩክሌር በስፋት ለሃይል ምንጭነት የሚጠቀሙ ሀገራትን ይመልከቱ፦