የኢትዮጵያና የአረብ ኤምሬትስ አየር ኃይሎች በጋራ ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት አቅርበዋል
88ኛው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን፤ በዛሬው እለትም “የጥቁር አንበሳ የአየር ትርዒት” የበዓሉ ድምቀት ነበር።
የተለያዩ የጦር አውሮፕላች፣ ጄቶችና ሄሊኮፕተሮችም “የጥቁር አንበሳ የአየር ትርዒት” የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን አሳይተዋል።
የኢትዮጵያና የአረብ ኤምሬትስ አየር ኃይሎች በጋራ ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው ብለዋል።
በሁሉም ዘርፍ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና መምራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም ስታውቀዋል።