በአውሮፓ ዋንጫ ስፔን ወደ ሩብ ፍጻሜ ስታልፍ ፈረንሳይ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች
ጀርመን ከእንግሊዝ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጉት ፍልሚያ የዛሬው ተጠባቂ ጨዋታ ነው
በትናንት በሁለት ጨዋታዎች ፍጹም ቅጣት ምትን ጨምሮ 23 ግቦች ከመረብ አርፈዋል
በመካሄድ ላይ የሚገኘው የአውሮፓ ዋንጫ ወደ ሩብ ፍጸሜ የሚያልፉ ብሄራዊ ቡድኖችን በመለየት ላይ የገኛል።
ትናንት ምሽት ወደ ሩብ ፍጻሜው ለማለፍ በተደረገው ፍልሚያም ፈረንሳይን ከስዊዘርላንድ፤ ስፔንን ከክሮሺያ ያገናኘ ነበር።
ፈረንሳይ ከስዊዘርላንድ ባደረጉት ጨዋታም የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ ፈረንሳይ በስዊዘርላንድ ተሸንፋ ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆናለች።
የጨዋታው መደበኛ ሰዓት 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በመለያ ምትም ስዊዘርላንድ 5ለ4 በሆነ ውጤት ፈረንሳይን መርታት ችላለች።
በጨዋታው ላይ ካሪም ቤንዜማ ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን በ57ኛው እና 57ኛው ደቂቃ እንዲሁም ፖል ፖግባ በ59ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።
ለስዊዘርላንድ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ ሴቭሮቪች በ15ኛው እና በጋቭራኖቪች በ90ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።
ሙሉ የጨዋታ ጊዜም 3ለ3 በሆነ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ፍቱም ቅጣት ምት ያመሩ ሲሆን፤ ኬሊያን ምባፔ የመታትን ኳስ የስዊዘርላንድ ግብ ጠባቂ በማዳኑ ፈረንሳይ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።
ሌላው ትናንት ምሽት በተካሄደው ጨዋታ ስፔን ከክሮሺያ ያደረጉት ጨዋታ ሲሆን፤ በጨዋታውም ስፔን ክሮሺያን በመርታት ወደ ሩብ ፍጻሜ መግባት ችላለች።
መደበኛ የጨዋታው ሰዓት 3 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ በተሰጠ ተጨማሪ ሰዓት ላይ ስፔን ባስቆጠረችው ሁለት ጎሎች በድምሩ 5ለ2 ክሮሺያን በመርታት ወደ ቀጣይ ዙር መግባቷን አረጋግጣለች።
በአውሮፓ ዋንጫ በእንግሊዝ እና በጀርመን መካከል ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ የሚደረገው ፍልሚያ ዛሬው ተጠባቂ ጨዋታ ሲሆን፤ ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ይሆናል።
ስዊድን ከዩክሬን ሌላኛው የዛሬ ምሽት ጨዋታ ሲሆን፤ ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚካሄድ መሆኑን የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።