ጤና ሚንስቴር “በጦርነትና ግጭቶች የወደሙ የጤና ተቋማትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ 3 ዓመት ይጠይቃል” አለ
በጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ
ከሰላም ስምምነት በኋላ ከ433 ሚሊየን በላይ ዋጋ ያላቸው መድሀኒትና የህክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ተልኳል
በጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በጦርነቱ በተጎዱ ክልሎች ውስጥ ስላሉ የጤና መሰረተ ልማት ጉዳት መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚንስትሯ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በትግራይ ፣አማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጤና መሰረተ ልማቶች መጎዳታቸውን ተናግረዋል።
- በአማራና በአፋር ክልሎች ከ1 ሺህ 400 በላይ የጤና ተቋማት መጎዳታቸውን የጤና ሚንስቴር አስታወቀ
- “ለታካሚዎቻችን መድሃኒት ለመስጠት ተቸግረናል” - የዓይደር ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር
በአምስቱ ክልሎች ያሉ የጤና መሰረተ ልማቶችን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ ሶስት ዓመት ይፈጃልም ብለዋል።
ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች ያሉ የጤና ተቋማትን ወደ ቀድሞ ይዘታቸው ለመመለስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግም ሚንስትሯ አክለዋል።
ሚንስትሯ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በትራይ ክልል ሰብዓዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት እና የጤናውን ስርዓት ወደነበረበት እንዲመለስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከጤና ሚንስቴርና ከተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ ከ30 በላይ ቡድን በ አላማጣ፤ ኮራም፤ ሽሬ፤ አክሱምና አድዋ ላይ በሁለት ዙር በማሳማራት ከሰላም ስምምናቱ ጀምሮ ስራዎችን እያገዙ ናቸው ተብላል።
በተመሳሳይ በተለያዩ ግዝያት ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፤ከ ደምና ቲሹ ባንክ፤ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከጤና ሚንስተር መሰረተ ልማት ዳይረክቶሬት የተዉጣጣ ቡድን በተቋማት ላይ የደረሰዉን የመስክ እያደረገ እንደሆነም ተጠቅሷል።
ቡድኑ እስካሁን በ33 የጤና ተቋማት ፤በአክሱም ደም ባንክ፤ እንዲሁም በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ ምልከታ አድርጓልም ተብሏል።
ምልከታ በተደረገባቸው ተቋማትም
በአላማጣና ሽሬ ኮሪዳር 12 ሆስፒታልና 28 ጤና ጣቢያዎች ካሉ ሰራተኞች ውስጥ ከ95% በላይ ያህሉ ወደ ስራ ተመልሰዋል።
የመድኃኒት እና ሕክምና ግብዓቶች ስርጭትንም በተመለከተ ከጎንደር መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ወደ ሽሬ ቅርንጫፍ በተለያዩ ዙሮች በተደረገ ጭነት 19 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የህይወት አድን መድኃኒቶችና የህክምና ግብዓትቶችን ሽሬና አቅራቢያው የሚገኙ ከተሞች ማድረስ ተችሏል ተብላል።
በተመሳሳይ ከደሴ ቅርንጫፍ ወደ አለማጣ እና በአካባቢዉ ላሉ ጤና ተቋማት 30 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የህይወት አድን መድኃኒቶችና የህክምና ግብዓትቶችም ተሰራጭተዋል ተብሏል።
እንዲሁም በክልሉ የደም ባንክ እጥረት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ከማዕከላዊ ደም ባንክ 200 ዩንት ደም መላኩ ተገልጿል።
በአጠቃላይ ወደ ትግራይ ክልል የጸረ-ወባ፣ የስኳር፣ የኩላሊት እጥበት፣ ፀረ-ቲቢ፣ ጸረ-ደምግፊት፣ የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የሚውሉ እና ሌሎች የህይወት አድን መድኃኒቶች ግምታቸው ብር ከ81 ሚሊዮን በላይ ዋጋ የሚያወጡ መድሀኒቶች በአለም ጤና ድርጅት እና ቀይ መስቀል በኩል ወደ መቀሌ ተልኳል።
በተጨማርም ለመደበኛ ክትበት አገልግሎት የሚዉሉ ግምታቸው ወደ ከ112 ሚሊዮን በላይ ዋጋ ያላቸው ክትባት ወደ መቀሌ መላክ እንደተላከ ሚንስትሯ ጠቅሰዋል።
በአጣቃላይ ከሰላም ስምምነቱ ቦኃላ ግምቱ ከ243 ሚሊዮን በላይ ወደ ሺሬና ከ194 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድሃንትና ሌሎች ግብዓቶች በመንግስት ማድረ ስ ተችሏል ተብላል።
በአጠቃላይ በመንግስትና በአጋር ድርጅቶች በኩል ወደ 1525 ሜትርክ ቶን ወደ መቀሌ የተለከ ስሆን ከዚህ ዉስጥ 1,200 ሜትርክ ቶን በላይ የሚሆነው በመንግስት ወደ መቀሌ የተደረገ ድጋፍ ነው ፡፡
በቀጣይም 10 ሜትሪክ ቶን የሚገመት መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ከመንግስት ወደ መቀሌ ለመላክ መዘጋጀቱንም ሚንስትሯ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።
በአማራ፣ አፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች
በለፉዉ አንድ ዓመት ዉስጥ በአማራና በአፋር ክልል ከተሰሩ የመልሶ ማቋቋምና ማደራጀት ስራዎች በአማራ ክልል 40 ሆሰፒታሎችና 415 ጤና ጣቢያዎችን አገልግሎት ማሰጀመር መቻሉ ተገልጿል።
በአፋር ክልልም አንድ ሆስፒታልና 20 ጤና ጣቢያዎች ስራ እንዲጀምሩ መደረጉ ሲገለጽ በኦሮሚያ ደግሞ 33 ጤና ጣቢያዎች ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ ተደርጓል ተብሏል።