“ለታካሚዎቻችን መድሃኒት ለመስጠት ተቸግረናል” - የዓይደር ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር
የሆስፒታሉ ስራ አሰኪያጅ የመብራት መቋረጥ ስራቸውን ከባድ እንዳደገባቸው ተናግረዋል
የሆስፒታሉ ሰራተኞች የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ቢሆኑም ደመወዝ ሳይከፋለቸው 16 ወራት ተቆጥረዋል
በመቀሌ የሚገኘው ዓይደር ሆስፒታል ለታካሚዎች መድሃኒት ለመስጠት እንደተቸገረ ሆስፒታሉ ገልጿል፡፡
በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራቸውም በርካታ ህሙማን በጤና ተቋማት ማግኘት የሚገባቸውን አግልግሎት እንዳያገኙ ያደረገ ከባድ ሁኔታ መፍጠሩ ዶ/ር ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡
ሁኔታው እንዳሳዘናቸው የተናገሩት የፌደራል መንግስት ትግራይ ተቆጣጥሮ ትግራይ በጊዜያዊ አስተዳደር በምጽመራበት ወቅት በክልል 80 በመቶ ውድመት አጋጥሟው እንደነር ጊዜያዊ አስተዳደሩ ማጥናቱን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ክብሮም በኢ-ሜይል ለአል-ዐይን አማርኛ በላኩት መልእክት እንደገለጹት “በተለይም ከሰኔ 21 ቀን 2013 (ህወሓት አብዛኛውን የትግራይ ግዛቶች መልሶ ከተቆጣጠረ በኋላ) ባለው የትራንስፖርት፣ የህክምና ቁሳቁሶች፣ አሌክትሪክ እና መድሃኒት ችግር ምክንያት የከባድ በሽታና ተመላላሽ ታካሚዎች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እያገኙ አይደለም፡፡”
ዋና ዳይሬክተሩ የሚመሩት ተቋም ዓይደር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንም አይነት መድሃኒት፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችና መድሃኖኒቶች የሚያገኝበት እድል ስሌለለ እንደ የዓለም ጤና ድርጅት እና ቀይ መስቀል በመሳሰሉ ለጋሽ ድርጅቶች ላይ ጥገኛ ሆኗል ብለዋል፡፡
ይህም ካለው የታካሚዎች ብዛት እንጻር አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በቂ እንዳልሆነ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
“የካንሰር፣ ወላዶች፣ የምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት እና ልጆች፣ ቀዶ ጥገና የሚደረግላቸው፣ ቃጠሎ የደረሰባቸው፣ ጽኑ ህሙማን፣ መተንፈስ ማይችሉ፣ የኩላሊት ጉዳት ያለባቸው፣ እንዲሁም የስኳር፣የልብ፣ የደም ግፊት እና ተመሳሳይ በሽታዎች ያሉባቸው ተመላላሽ ታካሚዎች አሉን፤ነገር ግን እንደ ድሮ መድሃኒት ለመስጠት ተቸግረናል”ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡
ቀደም ሲል ለሁለት ሶስት ወራት ለታካሚዎች ስንሰጥ የነበረው መድሃኒት አሁን ስሌለለን መድሃኒት የምንሰጠው ከአንድ ወር ለሚያንስ ጊዜ ብቻ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት በሚያጋጥሙ የድሮንና አውሮፕላን ጥቃቶች ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላችን የሚመጡ ታካሚዎች መኖራቸውንና እንደየ ጉዳታቸው መጠን እስከ ቀዶ ጥገና የሚደርስ የህክምና አገልገሎት ለመስጠት በሚደረገው ጥረት የግሉኮዝ፣ ፋሻ እና ህመም ማስታገሻ መድሃኒት እጥረት መኖሩም ገልጸዋል፡፡
ሌላው ከኤልክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጋር በያያዘ ያለው ችግር ከባድ መሆኑ ያነሱት ዶ/ር ክብሮም በመብራት መቋረጥ ምክንያት “ማሽኖቻችን ይቆማሉ፣ በቀዶ ጥገና እና የጽኒ ህሙማን ክፍል የሚገኙ በተለይም በማሽን መተንፈስ ያለባቸው ሰዎች ስለሚቋረጥባቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነን” ብለዋል፡፡
ሆስፒታሉ የፌዴራል ቢሆንም በጀት ሳያገኝ ድፍን ሁለት ዓመት እንደሆነው የተናገሩት ዋና ዳይሬከተሩ ለታካሚዎች ሲያቀርበው የነበረውን ምግብ በመቆሙ ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት መከሰቱ አንስተዋል፡፡
“ምግብ ገዝተን ለታካሚዎች ማቅረብ አልቻልንም፤ አሰካሁን የአከባቢው ህብረተሰብና ነጋዴዎች ካለቸቸው እያዋጡ በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚገኙ ታካሚዎች (እናቶች፣ ህጻናት፣ አባቶች) ምግብ ሲያቀርቡ የነበረ ቢሆኑም፤ አሁን እነሱም ችግር ውስጥ በመሆናቸው ምግብ ለማቅረብ ተቸግረናል” ሲሉም ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
በዓይደር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰሩ ዶክተሮቹ እና ነርሶች የፌደራሉ መንግስት ሰራተኞች ቢሆኑም ካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው በተለያየ መልኩ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
የህክምና ባለሙያዎቹና መላው የሆስፒታሉ ሰራተኞች ህይወት እጅግ ከባድ እንዳደረገው ዶ/ር ክብሮም ገ/ስላሴ ይናገራሉ፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ወዲህ ደመወዝ አግኝተው የማያውቁ የክልል ቢሮ ሰራተኞች እንዳሉ ሁሉ የዓይደር ሆስፒታል ሰራተኞችም ከግንቦት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 16 ወራት ምንም አይነት ደመወዝ አለማግኘታቸውም ገልጸዋል፡፡
ነገሩ ከባድ የሚደርገው ደግሞ ደመወዝ ብቻ ሳይሆን ሰራተኛው ለክፉ ቀን ብሎ በባንክ ሲቆጥብ ነበረውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እንዳይንቀሳቀስ መታገዱ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሆስፒታሉ ሰራተኞች “ከባድ መስዋዕትነት እከፈሉ ነው”ም ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ “ሰራተኞቹ ካለ ደመወዝና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሁም እየተራቡ በእግራቸው 10 ኪሎሜትሮች እየተጓዙ በከፍተኛ ኃላፊነትና ስነ-ምግባር ታካሚውን ለማገዝ ሌት ተቀን በመስራት ላይ ናቸው” ሲሉም የችግሩን መጠን እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል በጥቅምት 2013 የተደመረው ጦርነት እልባት በትግራይ የባንክ፣ የስልክ እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንደተቋረጡ ናቸው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) በትግራይ 5 ነጥብ አራት ሚሊዮን ህዝብ እርዳታ ፈላጊ መሆኑን ቀደም ሲል ገልጿል፡፡
በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ያለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የአፍሪካ ህብረት እና ምእራባውያን በርካታ ጥረት ቢያደርጉም ጦርነቱ በድጋሚ ሊቀሰቀስ ችሏል፡፡
ድርድሩን እንዲካሄድ ጥረት እያደረገ ያለው የአፍሪካ ህብረት መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ እንዲደራደር ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
ህብረቱ ያቀረበውን የተደራደሩ ጥሪ መንግስት እና ህወሓት መቀበላቸውን አስታውቀው ነበር፡፡ነገርግን በሎጂስቲክስ ምክንያት ሊካሄድ የነበረው ድርድር ተራዝሟል፡፡