ኢትዮጵያ የፀጥታው ም/ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያወጣው መግለጫ እንዳሳዘናት ገለፀች
ም/ቤቱ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ስር እንዲቀጥል መወሰኑን በበጎ እንደምትመለከትም ገለፀች
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ይታይ ሲል ትናንት መግለጫ አውጥቷል
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ይታይ ሲል ትናንት መግለጫ አውጥቷል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የህዳሴ ግድብን በተመለተ በተደረገው ውይይት ላይ ትናንት ማምሻውን ፕሬዚዳንታዊ መግለጫ አውጥቷል።
ምክር ቤቱ በመግለጫውም የህዳሴ ግድብ ድርድር ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ እና ድርድሩ በሶስቱ ሀገራት ማለትም በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን እንዲቀጥል መወሰኑን አስታውቋል።
- በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያሉ ልዩነቶች በውይይት መፈታት አለባቸው- የተመድ የጸጥታው ም/ቤት
- የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ቱኒዚያ ለፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ጠየቀች
ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሌሊት ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ በመግለጫውም የኢትዮጵያ መንግስት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ የሰጡትን መግለጫ መመልከቱን ጠቅሶ፤ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በህዳሴ ግድብ ላይ ክፍት ውይይት ከተደረገ ከ9 ሳምንታት በኋላ የተሰጠ መግለጫ ነው ብሏል።
የምክር ቤቱ አባላት የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ኢትዮጵያ በበጎነት እንደምትቀበለውም አስታውቋል።
ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ከተሰጠው ስልጣን ውጭ የውሃ መብት እና ልማት ጉዳይ ላይ መግለጫ ማውጣቱ እንዳሳዘነውም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመላክቷል።
ቱኒዚያ ምክር ቤቱ በህዳሴ ግድብ ላይ አቋም እንዲይዝ በማድረግ ታሪካዊ ስህተት ስርታለች ያለው ሚኒስቴሩ፤ በምክር ቤቱ ያለውን የአፍሪከ መቀመጫ ከግምት ያላስገባ ስራ ስርታለችም ብሏል።
“መግለጫው የምክር ቤቱ የአሠራር የሚፃረር መሆኑን በመጥቀስ ለማስተካከል የበኩላቸውን ሚና ለተጫወቱትን የምክር ቤት አባላት ኢትዮጵያ ታመሰግናለች” ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንታዊ መግለጫው መሠረት ሊነሱ የሚችሉ ማናቸውንም የይገባኛል ጥያቄዎች ኢትዮጵያ እንደማትቀበልም አስታውቃለች።