ኢትዮጵያ በሯን ለዓለም አቀፍ ባንኮች ክፍት እንደምታደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፁ
ባንክ የጥቂት ባለሀብቶች ብቻ መጠቀሚያ መሆን እንደሌለበት አስሳስበዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አዲሱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ መርቀው ከፍተዋል
ኢትዮጵያ በሯን ለዓለም አቀፍ ባንኮች ክፍት አንደምታደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን ያሉት ግዙህን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ ላለፉት 30 ዓመታት የውጪ ባንኮች እንዳይገቡ አስቀምጣው የነበረው ክልከላ ከዚህ በኋላ እንደማቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አንስተዋል።
ስለዚህ ባንኮች ለዚህ ዓለም አቀፍ ውድድር እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ለበርካቶች እንደ ትምህርት ቤት ያገለገለው የኢትዮፕያ ንግድ ባንክም እንደ ቀዳሚነቱ ለሌሎች ባንኮች ምሳሌ በሚሆን መልኩ እራሱን ለዓለም አቀፍ ውድድሩ እንዲያዘጋጅም መልእክት አስተላለፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በነግግግራቸው አከልውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዋርካ ነው ያሉ ሲሆን፤ ባንኩ ብዙዎችን የሙያ ባለቤት ያደረገና የአገር ባለውለታዎችን ያፈራ አንጋፋ ባንክ ነው ብለዋል።
ባንኩ በ80 ዓመታት ጉዞውም በበርካታ ውጣ ውረዶች ያለፈ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉንም በብቃት አልፎ እዚህ መድረሱንም ገልጸዋል።
ባንክ የጥቂት ባለሀብቶች ብቻ መጠቀሚያ መሆን የለበትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የብድር አሰጣጥ ስርዓቱ ላይ አርሶ እና አርብቶ አደሮችን በስፋት ማሳተፍ እንዳለበትም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ያስገነባውን ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ በዛሬው እለት አስመርቋል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ከመሬት በላይ 209 ነጥብ 15 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፤ ህንጻው 4 የምድር ውስጥ እና 49 ከምድር በላይ በድምሩ ባለ 53 ወለሎች ያሉት ሲሆን፤ በተጨማሪም ሁለት ባለ 11 እና ባለ 13 ወለሎች ግዙፍ ህንፃዎችን አካቷል።
በድምሩ ከ165 ሺህ ካሬሜትር በላይ ስፋት ላይ የተገነባው ህንጻው፤ 303 ሚሊየን 500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ ተደርጎበታል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ 5 አመት ከ11 ወር መውሰዱንም ከባንኩ ያገኘወ መረጃ ያመለክታል።