የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ዛሬ በተመረቀው የበርበራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስራ የጀመረ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሆነ
ኢትዮጵያን በሃርጌሳ በኩል ከበርበራ ወደብ የሚያገናኝ አውራ ጎዳና ግንባታ በማፋጠን ላይ ነው መባሉ ይታወሳል
የበርበራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዛሬ በፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ተመርቋል
ሶማሊላንድ በበርበራ አስፋፍታ በአዲስ ያስገነባችውን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አስመረቀች፡፡
በኤሚሬት መንግስት ድጋፍ የተገነባው አየር ማረፊያው ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 11 ቀን 2014 ዓ/ም በፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀሟና ቀጠናዊ አንድምታው
አየር ማረፊያው ከኢጋል ቀጥሎ ሁለተኛው የሃገሪቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ነው፡፡
አየር ማረፊያውን በይፋ መርቀው የከፈቱት ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ለሶማሊ ላንድ አዲስ የንግድ መግቢያ በር መሆኑን ገልጸዋል።
“ዛሬ ከአፍሪካ ግዙፍ አየር ማረፊያዎች አንዱን ነው ያስመረቅነው፤ ይህ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ዘመናዊ ሆኖ እንዲገነባ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሰውን የኤምሬትስ መንግስት እናመሰግናለን” ብለዋል ፕሬዝዳንት ቢሂ በንግግራቸው፡፡
ዲፒ ወርልድ በበርበራ ወደብ የሚገለገሉ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች የሚጠቀሙበትን አዲስ የበይነ መረብ የግብይት ስርዓት ይፋ አደረገ
ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያሟላው የኤርፖርቱ የመሠረተ ልማት ይዞታ፤ በአህጉሪቱ ካሉ መሰል ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች አንዱ እንደሚያደርገውም ነው የተናገሩት፡፡
የበርበራ አየር ማረፊያ በሶቪዬት ህብረት ነው እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ 4 ኪሎ ሜትር ገደማ ማኮብኮቢያ ኖሮት የተገነባው፡፡
በቀድሞው የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት መሃመድ ሲያድ ባሬ ይመራ የነበረው መንግስት እስከወደቀበት እስከ ፈረንጆቹ 1991 ድረስም፤ ከ1980ዎቹ ጀምሮ ተከራቶት ለነበረው ለአሜሪካ ጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) መንኮራኩሮች ድንገተኛ ማረፊያ ስፍራ ሆኖ ሲያገልግል ቆይቷል፡፡
ኢትዮጵያ ድርሻ ባላት በርበራ ወደብ መርከብ ማሰማራት ጀመረች
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ መልክ ተገንብቶና ማስፋፊያ ተደርጎለት ዛሬ ቅዳሜ ስራ በጀመረው በዚህ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያረፈና ስራ የጀመረ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሆኗል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያን በሃርጌሳ በኩል ዘምኖ ከተገነባው የበርበራ ወደብ ለማገናኘት የሚያስችል ባለ አራት መስመር አውራ ጎዳና ግንባታ በማፋጠን ላይ ነው መባሉ ይታወሳል፡፡