የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በበረራ ወቅት ጭስ እንዳጋጠመው አየርመንገዱ አስታወቀ
አየርመንገድ እንደገለጸው ጭሱ በምን ምክንያት እንደተከሰተ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ነው
አውሮፕላኑ ከሃዋሳ ወደ አዲስ አበባ እየበረረ በነበረበት ወቅት በካቢኑ ውስጥ ጭስ መታየቱን አየር መንገዱ አስታውቋል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በበረራ ወቅት ጭስ እንዳጋጠመው አየርመንገዱ አስታወቀ።
የበረራ ቁጥር ኢት/154/07 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከሃዋሳ ወደ አዲስ አበባ እየበረረ በነበረበት ወቅት በካቢኑ ውስጥ ጭስ መታየቱን አየር መንገዱ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።
አየር መንገዱ አውሮፕላኑ በተመደበለት ቦታ ማረፉን እና ተሳፋሪዎቹም በሰላም መውረዳቸውን ገልጿል።
አየርመንገዱ እንደገለጸው ጭሱ በምን ምክንያት እንደተከሰተ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ነው።
ከአምስት አመት በፊት ከአዲስ አበባ፣ ቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ ተነስቶ ወደ ኬንያ በማቅናት ላይ እያለ ቢሾፍቱ አካባቢ ከተከሰከሰው እና ለ157 ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነው የበራራ ቁጥር 302 ቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላን ወዲህ፣ በኢትዮጵያ አየርመንገድ አውርፕላኖች ላይ የከፋ አደጋ አላጋጠመም።