አቶ መስፍን የተሾሙት በኢትዮጵያ አየርመንገድ ኃላፊነት ለ11 አመታት ያገለገሉትን አቶ ተወልደን ተክተው ነው
የአቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነ መሾማቸውን የኢትዮጵያ አየርመንገድ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቆ ግርማ ዋቄ ለመገኛብዙሃን መሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣አቶ ታደሰ ጥላሁን፣አቶ ረታ መላኩ እና አቶ አለማየሁ አሰፋ የቦርድ አባል ሆነው መሾማቸውን አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየርመንገድ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ አቶ ግርማ ዋቄ የአየርመንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ተሾመዋል፡፡
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት፤ ላለፉት 11 አመታት አየርመንገዱን በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን በመተካት ነው፡፡ አቶ ተወልደ ከስራ ኃላፊነታቸው የለቀቁት በጤና እክል ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
በአየርመንገዱ ለ38 አመታት አገልግለዋል የተባሉት አዲሱ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በቶጎ የኤስካይ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል ተብሏል፡፡