ፈረንሳይ በእስራኤል ስፖርተኞች ላይ የደረሰውን የግድያ ዛቻ እየመረመረች ነው
ባለፈው ጥቅምት ወር የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በበርካታ ሀገራት ጸረ-እስራኤል እና እስራኤላውያን ተቃውሞዎች ተካሂደዋል
ሽብርተኞች የፓሪስ ኦሎምፒክን ሊረብሹ ይችላሉ የሚል ስጋት ያላት ፈረንሳይ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችን ጨዋታዎቹ በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች አሰማርታለች
ፈረንሳይ በእስራኤል ስፖርተኞች ላይ የደረሰውን የግድያ ዛቻ እየመረመረች ነው።
የፈረንሳይ ፖሊስ በፓሪስ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ በሚሳተፉ ሶስት የእስራኤል ስፖርተኞች ላይ የደረሰውን የግድያ ዛቻ እየመረመረው እንደሚገኝ የፓሪስ አቃቤ ህግ ቢሮ በዛሬው እለት አስታውቋል።
የጸረ-ሳይበር ወንጀል ፖሊሶችም ባለፈው አርብ እለት የስፖርተኞች የግል መረጃዎች እንዴት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እንደተለቀቁ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን እና መረጃዎቹም እንዲሰረዙ እንደሚፈልግ አቃቤህጉ ገልጿል።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፓሪስ ኦሎምፒክ የእስራኤል ስፖርተኞችን እና ጎብኝዎችን ኢላማ ያደረገ በኢራን የሚደገፍ ሴራ ሊኖር እንደሚችል የፈረንሳይ አቻቸውን ባለፈው ሀሙስ እለት አስጠንቅቀው ነበር።
በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ የእስራኤል ስፖርተኞች የ24 ሰአታት ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው። የእስራኤል የሀገር ውስጥ የደህንነት አገልግሎት ሸን ቤት ለእስራኤል የኦሎምፒክ የልኡክ ቡድን ጥበቃ ለሚያደርጉት የፈረንሳይ የጸጥታ ኃይሎች ድጋፍ እያደረገ ነው።
ባለፈው ጥቅምት ወር የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በበርካታ ሀገራት ጸረ-እስራኤል እና እስራኤላውያን ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።
ሽብርተኞች የፓሪስ ኦሎምፒክን ሊረብሹ ይችላሉ የሚል ስጋት ያላት ፈረንሳይ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችን ጨዋታዎቹ በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች አሰማርታለች።
የፓሪስ ኦሎሞፒክ ውድድር ባለፈው አርብ እለት በፈረንሳይ ፓሪስ በይፋ ተከፍቷል።