አየር መንገዱ ባለፉት 25 ዓመታት ለአሜሪካ ማህበተሰብ ለሰጠው አገልግሎት ሽልማቱ ተበርክቶለታል
የአሜሪካው ፐሬዝዳንት ጆ ባይደን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት ዘመን ሽልማት አበረከቱ።
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክታለች።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለአሜሪካዊያን አገልግሎት የሰጡ ተቋማትን እና ግለሰቦችን የህይወት ዘመን ሽልማት ይሰጣል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 25 ዓመታት በአሜሪካ ለሚኖሩ ዜጎች በሰጠው አገልግሎት የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኗል።
አየር መንገዱ ሽልማቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ "ሽልማቱ ለሰጠው አገልግሎት እውቅና የሰጠ ነው" ብሏል።
ፕሬዝዳንት ባይደን የፈረሙበት ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች በአትላንታ በተዘጋጀ መርሀግብር ላይ ተቀብለዋል ተብላል።
የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ሽልማቱ ባለፉት ዓመታት ለሰጠው የአቪዬሽን አገልግሎት እውቅና ባለፈ ዓለም አቀፍ ትብብሮችን እንዲያሰፋ ያደርጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ በሳምንት 30 በረራዎችን ወደ አሜሪካ ዋና ዋና ከተሞች በረራዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።
በ2016 በጀት ዓመት 7ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘ የገለጸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት 17 ሚሊዮን መንገደኞችንም እንዳስተናገደ አስታውቋል