የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል አቋርጦት የነበረውን በረራ እንደሚጀምር ገለጸ
አየር መንገዱ በአካባቢው ባለው ጦርነት ምክንያት ነበር ከ40 ቀን በፊት ነበር በረራውን ያቋረጠው
የዓለምን ትኩረት ስቦ የነበረው የእስራኤል-ፍልስጤም ጦርነት ከ46 ቀን በኋላ የተኪስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል አቋርጦት የነበረውን በረራ እንደሚጀምር ገለጸ፡፡
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከተጀመረ 47ኛ ቀኑን ይዟል።
ከሁለቱም ወገን 15 ሺህ ገደማ ሰዎች የተገደሉበት ይህ ጦርነት እንዲቆም በርካቶች ሲያሳስቡ ቢቆዩም ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን አየር መንገዶች ወደ እስራኤል ሲያደርጉት የነበረውን በረራ አቋርጠው ቆይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን በረራ ዳግም እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ አክሎም በሳምንት አምስት ቀናት ከአዲስ አበባ-ቴልአቪቭ ከተማ የቀጥታ በረራውን እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡
የደርሶ መልስ ትራንስፖርት አገልግሎቱን በበረራ መስመር ኢት 404 እና 405 አውሮፕላኖቹ እንደሚሰጥ የገለጸው አየር መንገዱ ሁሉንም የሳምንቱ ቀናት አገልግሎቱን እሰጣለሁም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ 67 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማማ
ከዚህ በፊት ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ አልያም ከአዲስ አበባ ቴልአቪቭ ለመብረር የጉዞ ቲኬት የገዙ ደንበኞች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የበረራ ማስተካከያዎችን ማድረግ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡
እንዲሁም የቲኬት ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው የሚፈልጉ ሰዎች ያለምንም ቅጣት እንመልሳለን ያለው አየር መንገዱ ደንበኞች የበረራቸውን ጊዜ ማራዘም ከፈለጉም እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ቀናት ድረስ ማራዘም ይችላሉ ሲልም ገልጿል፡፡