በጭጋጋማ አየር ምክንያት የበረራዎች ማረፊያን ማዛወሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ
አየር መንገዱ “ከቁጥጥራችን በላይ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን” ሲል ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቀዋል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገዶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል
በአዲስ አበባ ባለው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት የበረራዎች ማሪፊያን ማዛወሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና አካባቢው ጭጋጋማ የአየር ጠባይ መኖሩን ገልጾ፤ ከብዙ ጥንቃቄዎች ጋር ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑ በረራዎች ወደ ቅርብ አየር ማረፊያዎች እንዲዛወሩ ተደረገዋል ብሏል፡፡
ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ስለሆነ ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አሁን በአማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች እያረፉ፤ የአየር ሁኔታው ሲሻሻል ወደነበረበት ይመለሳሉም ነው ያለው አየር መንገዱ፡፡
ደንበኞቹን “ከቁጥጥራችን በላይ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን” ያለው አየር መንገዱ ስለ በረራዎቹ ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ለደንበኞቹ በየጊዜው እንደሚያስታውቅም ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገዶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አለምአቀፍ የአየር ትራንስፓርት ማህበር (IATA) ባወጣው የአሀዝ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጓጓዘው የመንገደኛ ብዛት ከምርጥ 200 አየር መንገዶች የ 20ኛ ደረጃን አግኝቷል።
በተመሳሳይም አየር መንገዱ አባል የሆነበት ስታር አሊያንስ ቡድንም “የ2020 ምርጥ የአየር መንገዶች ህብረት” ሽልማትን ለመቀዳጀት መብቃቱ የሚታወስ ነው። አየርመንገዱ ባለፈው አመትም ዲኬድ ኦፍ ኤክሰለት አዋርድ የተባለ ሽልማት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡