በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሰላም ስምምነት ህወሓት ትጥቅ ለመፍታት ተስማምቷል
የፌደራል መንግስት እና ህወሃት ወታድራዊ አዛዦች ህወሃት ትጥቅ የሚፈታበት መንገድ ላይ በኬንያ ናይሮቢ ምክክር ማደረግ ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኢታምዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጀነራል ታደስ ናቸው እየተነጋገሩ ያሉት ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ውይይቱ ሁለቱ የጦር አመራሮች በደቡብ አፍሪካ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ነው ምክክር የጀመሩት።
በስምምነቱ አንቅጽ 6 ሁለቱ ሃይላት ስምምነቱ በተፈረመ በአምስት ቀናት ውስጥ የህወሃትን ትጥቅ ማስፈታት ጨምሮ ዘላቂ ስላምን ማሰፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ የጦር አመራሮች ይመክራሉ ይላል።
ዛሬ የጀመረው ውይይት በትግራይ አስችኳይ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር ተከፍቶ የተቋርጡ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ምክክር ይደረግብታል ብሏል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መግለጫ።
ሁለቱ የጦር መሪዎች የናይሮቢው ውይይት ከመጀመራቸው በፊት የኮሙዩኒኬሽን መስመር መዘርጋታቸው ይታወሳል።
በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለው ንግግር ለቀጣይ ቀናትም ይቀጥላል ተብሏል።
በደቡብ አፍሪካ በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት ህወሓት ታጣቂዎቹ ትጥቅ እንዲፈቱ መስማማቱ ይታወሳል።