የአሜሪካው የጃክፖት ሎተሪ የሚያስገኘው 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር የአለም ክብረወሰን ሆኖ ተመዘገበ
በዛሬው እለት የሚወጣው የሎተሪ እጣ ለሶስት ወራት 39 ጊዜ ዕጣው ቢወጣም አሸናፊ አልተገኘለትም
ሎተሪውን የሚያሸንፉ ግለሰቦች የሚደርሳቸው ገንዘብ 929 ሚሊየን ዶላር ነው
የአሜሪካው "ፓወርቦል" የጃክፖት ሎተሪ የሚያስገኘው 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዝግቧል፡፡
በዛሬው እለት የሚወጣው የሎተሪ እጣ ለሶስት ወራት 39 ጊዜ ዕጣው ቢወጣም አሸናፊ አልተገኘለትም።
ቅዳሜ ጥቅምት 26 በወጣው እጣም 1 ነጥብ 5ቢሊየን ዶላር የሚያስገኘውን አሸናፊ ቁጥር የያዘ ግለሰብ ሳይገኝ ቀርቷል። አሸናፊውን ቁጥር የማግኘት እድሉ ከ292 ነጥብ 2 ሚሊየን አንድ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
የፓወርቦል ሎተሪውን የቆረጡ ሰዎች የገዙት የሎተሪ ትኬት ስድስት ቁጥሮች ከአሸናፊው ቁጥር ጋር አንድ አይነት ከሆኑ ብቻ ነው ከፍተኛውን ሽልማት የሚወስዱት።
የአለማችን ትልቁ የጃክፓት ሽልማት ክብረወሰን በፈረንጆቹ 2016 ሲሰበር ሶስት የፓወርቦል አሸናፊዎች 1 ነጥብ 57 ቢሊየን ዶላር ተካፍለዋል።
በ2 ዶላር በሚገዙ የፓወርቦል ትኬቶች አሸናፊ የሚሆኑት ግለሰቦች ገንዘቡን በአንድ ጊዜ አልያም በ29 አመት ውስጥ እየቀናነሱ መውሰድ ይችላሉ።
ሎተሪውን የሚያሸንፉ ግለሰቦች የሚደርሳቸው ገንዘብ 929 ሚሊየን ዶላር ነው።
በዚሁ ተመሳሳይ ሎተሪ ከስምንት ዓመት በፊት በወጣ ዕጣ ሦስት ባለዕድሎች ከፍተኛ የተባለውን ክብረ ወሰን 1 ነጥብ 59 ቢሊዮን ዶላር አሸንፈው ተካፍለው ነበር።
በፈረንጆቹ 1992 የተጀመረው የፓወርቦል ጃክፖት ሎተሪ፥ ዋሽንግተንን ጨምሮ በ45 የአሜሪካ ግዛቶች ይሸጣል።