አልኮል ጠጥተው ሲጨፍሩ አደሩ” በሚል በስነ-ምግባር ጉድለት የተከሰሱት የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጻ ተባሉ
የጠቅላይ ሚኒስትሯ ድርጊት “ የፊንላንድን ክብር የሚነካ” ነው በማለት በርካቶች ቅሬታቸውን ገልጸዋል
ወጣቷ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲጨፍሩ አደገኛ እጽ አለመውሰዳቸው በምርመራ መረጋገጡ ይታወሳል
ባለፈው ነሐሴ ወር የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን “አልኮል ጠጥተው ከጓደኞቻቸው ጋር ሲጨፍሩ የሚያሳይ ቪዲዮ” ሾልኮ ከወጣ በኋላ ጉዳዩ አነጋገሪ ሆኖ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡
በርካቶችም የጠቅላይ ሚኒስትሯ ድርጊት “ የፊንላንድን ክብር የሚነካ” ነው በማለት ቅሬታቸው ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡
በዚህም የ35 ዓመቷ ሳና ማሪን ከአንድ የሀገር መሪ የማይጠበቅ የስነ ምግባር ጉድለት አሳይቷል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ራሳቸው ሲከላለከሉ ከቆዩ በኋላ አሁን ላይ ነጻ መባላቸው በመነገር ላይ ነው፡፡
የሀገሪቱ የፍትህ ሚኒስትር ቶማስ ፖይስቲ የጠቅላይ ሚኒስትሯ ድርጊት ኃላፊነታቸው ከመዘንጋት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል፡፡
ፖይስቲ “ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ህጋዊ ያልሆነ ነገር ስለመፈጸማቸው ወይም ኃላፊነታቸውን ስለመዘንጋታቸው የቀረበውን ክስ ሊያሟግት የሚችል ምንም ምክንያት የለም ”ሲሉም አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀገሪቱ ተቃዋሚዎቹች ጠቅላይ ሚኒስትሯ ያደረጉት ድርጊት አርዓያ እንዳልሆነ ስልጣን እንዲለቁ ቢጠይቁም የ36 አመቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪና ግን “አደንዛዥ ዕጽ አልወሰድኩም” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በዚህም የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች፤ አደንዛዥ ዕጽ ወስደው ከነበረ ምርመራ እንዲያደርጉ በጠየቁት መሰረት ወጣቷ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን አደገኛ እጽ አለመውሰዳቸው ቀደም ሲል በምርመራ መረጋገጡ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ከምርመራ ውጤት ይፋ መሆን በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሯ “በህይወቴ አደገኛ እጽ የሚባል ወስጄም አፌ ውስጥም ገብቶ አያውቅም“ ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
በሞቀ ጭፈራ ላይ እንደነበሩ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪና የ”አልኮል መጠጥ” መውሰዳቸውን ግን አልሸሸገችም፡፡
ማሪና በወቅቱ ከጓደኞቻቸው ጋር በሞቅታ ሲጨፍሩ የሚያሳው ቪዲዮ ሾልኮ በመውጣቱ መበሳጨታቸው ቢገልጹም፤ የሚቀርቡ ትችቶች ሚዛናዊ አይደሉም ብለዋል፡፡
"ደንሻለሁ፣ ዘፍኛለሁ እንዲሁም ተዝናኝቻለሁ - ይህ ፍጹም ህጋዊ ነገር ነው " ሲሉም ነበር ለቀረቡላቸው ትችቶች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሯ፡፡
ሳና ማሪን ለጋዜጠኖች በሰጡት አስተያየት " የቤተሰብ ህይወት አለኝ ፤ የስራ ህይወት አለኝ፤ ከጓደኞቼ ጋር የምዝናናበት ጊዜም አለኝ፡፡ እንደ ማንም ሰው ለመዝናነት በትክክለኛው የእድሜ ክልል የምገኝ ሰው ነኝ" የሚል መከራከሪያም አቅርበው ነበር፡፡
የግል ባህሪያቸው እንዲቀይሩ የመፈለጉ ጉዳይ ትልቅ ቁም ነገር እንዳልሆነ የሚመጉትት ጠቅላይ ሚኒስትሯ፤" የምለውጠው ነገር የለም ይህንኑ ባህሪይ እቀጥልበታለሁ፤ይህ (ባህሪይ) ተቀባይነት እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉም አክላለች።
ከሁለት አመታት በፊት የ34 አመት ወጣት ሳሉ የፊንላንድ ከፍተኛው የመሪነት በትረስልጣን የጨበጠችው ሳና ማሪን በጣም ዘናጭና ለጥባብ ባላት ፍቅር ብዙውን ጊዜ ጭፈራ ባለባቸው ስፍራዎችና ፌስቲቫሎች የመታየት ልምድ እንዳላቸው ይነገርላቸዋል፡
ባለፈው አመት የኮቪድ ሰላባ ከሆኑ ሰዎች ጋር ተገናኝተው ሲያበቁ ወደ ምሽት ክለብ በመሄዳቸው ይቅርታ አስከመጠየቅ የደረሱበት አጋጣሚም ይታወሳል፡፡