አትሌቶቹ አበረታች ቅመሞችን ወስደው በመገኘታቸው እስከ አራት ዓመታት የሚቆይ እገዳ ተጥሎባቸዋል ተብሏል
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ፡፡
የአለም አትሌቲክስ እና ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመምች ህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልጿል።
የቅጣት ውሳኔው ከተላለፈባቸው አትሌቶች መካከል አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ ፣ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን እና አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ሲሆኑ የአበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት መፈጸማቸው ተረጋግጧል ተብሏል።
ጥሰቱን ተከትሎም አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ የካቲት 2015 ዓ.ም በተካሄደው ምርመራ ኢፒኦ የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡
በዚህም መሰረት አትሌት ሳሙኤል አባተ ለ2 ዓመታት ማለትም እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ድረስ በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡
አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት (ABP) ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ የተረጋገጠባት ሌላኛዋ ኢትዮጵያ አትሌት ስትሆን ለአራት ዓመታት እገዳ ተጥሎባታል ተብሏል፡፡
በፓሪስ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድሩን እንዳጠናቅቅ ያደረገኝ የሀገሬ ፍቅር ነው - አትሌት ቀነኒሳ
አትሌቷ ከህዳር 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 2019 ዓ.ም ድረስ ለአራት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ ቅጣት እንደተጣለባት ውሳኔውን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ቻይና ሀገር ውስጥ በነበረው ውድድር ላይ በተካሄደው ምርመራ ትሪያምሲቦሎን አሴቶናይድ የተባለውን በውድድር ወቅት የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሟ በመረጋገጡ ለ2 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ ቅጣት ተጥሎባታል፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት አትሌት ሹሜ ጣፋ ደስታ እና አትሌት መንግስቱ በቀለ ተዴቻ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ ተጠቅመው ተገኝተዋል በሚል እስከ አራት ዓመታት የሚዘልቅ እገዳ መጣሉ ይታወሳል፡፡