ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ የፓሪስ ማራቶንን አሸነፉ
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ልዑል ገ/ስላሴ ደግሞ 2:04:07 በመግባት 3ኛ ሆኗል
ታምራት ቶላም የራሱን እና የውድድሩን ሪከርድ በማሻሻል የአምስተርዳም ማራቶንን አሸንፏል
ሴት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ የፓሪስ ማራቶንን አሸነፉ፡፡
ዛሬ በተካሄደው የፓሪስ ማራቶን ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን በማሸነፍ ሴት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ነግሰዋል፡፡
ትዕግስት ማሙዬ ውድድሩን በአንደኛነት ስታሸንፍ የኔነሽ ድንቄሳ እና ፋንቱ ጂማ በሰከንዶች ተለያይተው ተከትለዋት ገብተዋል፡፡
ኬንያዊው ኤሊሻ ሮቲች በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረውን የውድድሩን ሪከርድ አሻሽሎ ባሸነፈበት የወንዶቹ ውድድር ደግሞ ሃይለማርያም ኪሮስ ሁለተኛ ሆኗል፡፡
አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች
በሌላ ተያያዥ የአትሌቲክስ ዜና ታምራት ቶላ የራሱን እና የውድድሩን ሪከርድ በማሻሻል ዛሬ በሆላንድ አምስተርዳም ለ45ኛ ጊዜ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር አሸነፈ፡፡
ታምራት ኬንያዊው ላውረንስ ቼሮኖ ከ3 ዓመታት በፊት ይዞት የነበረውን የውድድሩን ሪከርድ ( 2.04.06 ) በማሻሻል እና 2.03.38 በመግባት ነው ያሸነፈው፡፡
ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች
በ2016ቱ የሪዮ ኦሎምፒክ በ10 ሺ ሜትር የነሃስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው ታምራት የዱባይ ማራቶን አሸናፊ መሆኑም ይታወሳል፡፡
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ልዑል ገ/ስላሴ ኬንያዊውን በርናርድ ኮኤችን ተከትሎ 2:04:07 በመግባት 3ኛ ሆኗል፡፡
ገበያነሽ ሃይሉ እና ወርቅነሽ ዓለሙ ደግሞ 3ኛ እና 4ኛ በመሆን የሴቶች ማራቶንን አጠናቀዋል፡፡