የአፍሪካ የስነ ጽሁፍ ሽልማት መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገ ደራሲዎችን የሚሸልም ተቋም ነው
በኢትዮጵያ ተወልዳ በአሜሪካ ያደረገችው ሜሮን ሀደሮ በአጫጭር የስነ ጽሁፍ ዘርፍ ሽልማትን ስታሸንፍ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ተብላለች።
ደራሲ ሜሮን ሽልማቱን ካሸነፈች በኋላ እንዳለችው በደስታ ድንጋጤ ውስጥ መሆኗን ገልጻ የመጨረሻዎቹ እጩ ውስጥ መግባቴ በራሱ ትልቅ ክብር ነበር ስትል ተናግራለች።
ደራሲ ሜሮንን የዚህ አሸናፊ ያደረጋት አጭር ታሪክ ጌቱ የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ በአዲስ አበባ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና የውጭ ለጋሽ ድርጅቶች ዕርዳታ ተለዋዋጭ እንቅስቃሴዎችን የሚዳስስበት አጭር ድርሰት ነው።
የድርሰቱ ጭብጥ የዳኞችን ትኩረት በመሳቡ ሽልማቱን አሸናፊ ሳያደርጋት እንዳልቀረም ደራሲዋ ለቢቢሲ ተናግራለች።
ስለስደተኞች እና የመፈናቀል አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ታሪኮች ሁሌም ስሜቷን እንደሚገዛት የተናገረችው ደራሲ ሜሮን ሽልማቱን ማሸነፏን ተከትሎ 10 ሺህ ዩሮ ወይም 13 ሺህ ዶላር እንደምታገኝ ተገልጿል።
በህክምና ሙያ ከተሰማሩ ወላጆቿ የተገኘችው ደራሲ ሜሮን የድምጻዊ መክሊት ሀደሮ እህት እንደሆነችም ተዘግቧል።ሁለቱም ወላጆቿ የህክምና ዶክተሮች ሲሆኑ የድምፃዊት መክሊት ሀደሮ እህት ነች።ለስኬቴ የመክሊት እገዛ ከፍተኛ ነበር ስትል ተናግራለች።
የኬን አፍሪካ ደራሲያን ሽልማት በፈረንጆቹ 200 በእንግሊዝ አገር የተመሰረተ ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚጻፉ የስነ ጽሁፍ ስራዎችን እያወዳደረ በየዓመቱ ለደራሲዎች የሚሸልም ተቋም ነው።
አሁን ላይ አኮ ኬን ሽልማት የቀድሞው የቡከር ግሩፕ ፒኤልሲ ሊቀመንበር የነበሩትን ሰር ሚካኤል ሃሪስ ኬንን ለማሰብ ታስቦ የሚዘጋጅ ሽልማት ነው።