አሜሪካ በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጵያን፣ ግብፅንና ሱዳንን የሚያስማማ መፍትሄ ላይ እንዲደረስ ትፈልጋለች- ማይክ ፖምፒዮ
ለሶስቱም ሀገራት የሚሆን መፍትሄ እንዲመጣ እንፈልጋልን-ፖምፒዮ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ውይይት ለሶስቱም ሀገራት ማለትም ለኢትዮጵያ፣ ለግብፅና ለሱዳን የሚበጅ መፍትሄ ላይ እንዲደረስ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡
ፖምፒዮ ይህን ያሉት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነበር፡፡
እስካሁን በግድቡ ላይ እየተካሄደ ያለው ዉይይትም ሙያዊ ነበር ብለዋል፡፡
ሽብርና የአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር እንሰራልን ያሉት ፖምፒዮ ለኢትዮጵያና ለሶማሊያ ተጨማሪ እርዳት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ በበኩላቸው ከአሜሪካ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ እንደሚሰሩ እንዲሁም አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እንደምትደግፍ ፖምፒዮ እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ አሜሪካ በግድቡ ድርድር ዙሪያ እየተወጣች ላለው ሚናም አመስግነዋል፡፡