የጥምቀት በዓል አከባበር በምስል
በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ፣ በጎንደር፣ በማይጨው፣ በጋምቤላ፣ በባቱና የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍልች ስርአተ ጥምቀቱ ተከናውኗል
የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ የሚከበር በዓል ነው
የጥምቀት በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሯል።
በመላ ሀገሪቱ ትናንት ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ በመውረድ በዚያው ማደራቸው ይታወቃል።
ዛሬ ማለዳ በዓሉ ታቦታቱ ባደሩባቸው ጥምቀተ ባህር የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከናውነው ስርዓት ጥምቀት ተካሂዷል።
በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የጥምቀት በዓል ሲከበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የጥምቀት ስርአተ ጸሎትን መርተው ባህረ ጥምቀቱን ባርከዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ነው የተከበረው።
44 ታቦታት ከአድባራት የሚወጡባት ጎንደርም የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከብሮባታል።
በዓሉ በባህር ዳር፣ በሃዋሳ፣ በጅማ፣ በሻሸመኔ፣ በሆሳዕና፣ በባቱ፣ በደብረ ብርሃን፣ በነቀምቴ፣ በጋምቤላ ፣ በማይጨው ፣ ላሊበላና በተለያዩ አካባቢዎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱንና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሯል።
የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር በዓል ነው።