ኔቶ በአስርት አመታት ውስጥ ትልቅ የተባለ ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂድ መሆኑን ገለጸ
ኔቶ ልምምድ የሚያደርገው ሩሲያ አባል ሀገርን እንዳታጠቃ ሩሲያን ለማስፈራራት ነው
ኔቶ እንደ ድርጅት በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት በቀጥታ አይሳተፍ እንጅ አባል ሀገራት በተናጠል እና በቡድን በመሆን ለኪቭ የጦር መሳሪያ ድጋፍ አድርገዋል
ኔቶ በአስርት አመታት ውስጥ ትልቅ የተባለ ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂድ መሆኑን ገለጸ።
የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነው ኔቶ በቀጣይ ሳምንት 90ሺ ወታደሮችን በማሳተፍ በአስርት አመታት ውስጥ ትልቅ የሚባል ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂድ መሆኑን ገልጿል።
የኔቶ ልምምድ የሚካሄደው ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለው ጦርነት ባለበት የመቆም አዝማሚያ ማሳየቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።
ኔቶ እንደ ድርጅት በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት በቀጥታ አይሳተፍ እንጅ አባል ሀገራት በተናጠል እና በቡድን በመሆን ለኪቭ የጦር መሳሪያ ድጋፍ አድርገዋል።
ኔቶ፣የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በፈረንጆቹ የካቲት 2022 ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ከማዝመታቸው በፊት በሩሲያ ምስራቅ አቅጣጫ ጦሩን አከማችቶ ነበር።
ኔቶ ልምምድ የሚያደርገው ሩሲያ አባል ሀገርን እንዳታጠቃ ሩሲያን ለማስፈራራት ነው።
ወታደራዊ ጦምረቱ እንዳለው በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረገው የኔቶ ወታደራዊ ልምምድ "ስቲድፋስት ዲፌንደር 24" የተሰኘ ሲሆን ይህም ውስብስብ ወታደራዊ ዘመቻን በሰፊ ቦታ ማካሄድ እንደሚችል ለማሳየት ያለመ ነው።
እስከ ግንቦት በሚካሄደው ልምምድ፣ ወታደሮች ሊከሰቱ የሚችሉ ጥቃቶችን እንዴት መመከት እንደሚችሉ ይለማመዳሉ።
በኔቶ የመከላከል እቅድ መሰረት ሩሲያ እና የሽብር ድርጅቶች የኔቶ ዋና ተቀናቃኝ ናቸው።
በዚህ ልምምድ ጥምረቱ የኢዩሮ አትላንቲክ አካባቢን ለመጠበቅ የሚያሰችለውን አቅም ያሳያል ተብሏል።