የጄነራል ሃፍታር ጦር የሲርጥ ከተማን መቆጣጠሩን አስታውቋል
መቀመጫውን በምስራቃዊ ሊቢያ ቶብሩክ ያደረገው የጄነራል ከሊፋ ሃፍታር ጦር ስትራቴጂካዊቷን የወደብ ከተማ ሲርጥን መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡
የጦሩ ቃል አቀባይ ካሊድ አል ማህዩብ በከተማዋ የሚገኘውን የአል-ቃርዳቢያ አየር ማረፊያን ጨምሮ የከተማዋን ቁልፍ ቦታዎች ተቆጣጥረናል ማለታቸውን የዘገበው ሲጂቲኤን አፍሪካ ነው፡፡
የቀድሞው የሃገሪቱ መሪ ሙአማር ጋዳፊ የትውልድ ስፍራ ስለመሆኗ የሚነገርላት ሲርጥ መቀመጫውን ትሪፖሊ ባደረገውና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንዳለው በሚነገርለት የጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል ሳራጅ ጦር ቁጥጥር ስር ነበረች፡፡
ቱርክ የጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል ሳራጅን ጦር የሚደግፉ ወታደሮችን ለመላክ ስለመወሰኗ ከሰሞኑ ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡