ወደ እስራኤል ለመድረስ በሱዳን በረሃ በእግር ጉዞ ላይ ሳሉ ህይወታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ትናንት በእየሩሳሌም ታስበዋል
ወደ እስራዔል በመጓዝ ላይ ሳሉ በሱዳን በረሃዎች ህይወታቸው ላለፈ ቤተ እስራኤላውያን መታሰቢያ ተደረገ
ወደ እስራኤል ለመድረስ በሱዳን በረሃ በእግር ጉዞ ላይ ሳሉ ህይወታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ትናንት በእየሩሳሌም ታስበዋል።
ቤተ እስራኤላውያኑ የከፈሉት የሕይወት መስዋዕትነት የሚዘከርበት ይህ የመታሰቢያ መርሐ ግብር በየዓመቱ ግንቦት 13 በሃገሪቱ መንግስት የሚከበር ሲሆን በትናንቱ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ሩቨን ሪቭሊን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡
ከሰሞኑ በአዲስ ገቢዎች ጉዳይ (አልያና ክሊታ) ሚኒስትርነት እና በአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሚኒስትርነት የተሾሙት ወይዘሮ ፕኒና ታምኖ እሸቴ እና አቶ ጋዲ ይባርከኝ እንዲሁም በእስራኤል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ረታ ዓለሙም በመርሐ ግብሩ ላይ ነበሩ፡፡
የቤተ-እስራኤል የሃይማኖት አባቶችና የማህበረሰቡ ተወካዮች እንዲሁም የሃገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች የተገኙም ሲሆን ታዋቂዋ ድምፃዊ ኤደን አለነ ሰለመታሰቢያው ሙዚቃ ስለማቅረባቸው በእስራኤል ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመታሰቢያ መርሃ-ግብሩ በዓላማ የመጽናትን አርዓያነት ለወጣቱ የሚያሳይ ነው ያለው ኤምባሲው የማህበረሰቡ ዓላማ እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም አስታውቋል።