ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምትጠብቅበት የወንዶች 10000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል
በ3000 ሜትር ወንችና በ800 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውን አትሌቶች ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል
የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ውድድሮች ሌሊት ላይ ተጀምረዋል
የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ውድድሮች ሌሊት ላይ የጀመሩ ሲሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተሳተፉባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ውጤቶች ተመዝግበዋል
በዚህም መሰረት በ3000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ
1. ለሜቻ ግርማ በ8 ደቂቃ፣ ከ09 ሰከንድ፣ ከ83 ማይክሮ ሰከንድ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ማጣሪያውን አልፏል።
2. ጌትነት ዋለ በ8 ደቂቃ፣ ከ12 ሰከንድ፣ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ በመግባ 2ኛ በመውጣት ማጣሪያውን አልፏል።
አትሌት ታደሰ ታከለ በ8:24.69 ሰዓት 8ኛ ይዞ በማጠናቀቁ ማጣሪያውን ማፍ እንዳልቻለም ከስፍራው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
በ800 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድርም አትሌት ሀብታ ሀብታም አለሙ በ2 ደቂቃ፣ ከ01 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰክንድ ሰዓት በመግባ 2ኛ ደረጃ ማጣሪያውን አልፋለች።
ዛሬ አርብ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የሚጠበቅበት የወንዶች 10000 ሜትር የፍጻሜ ውድድር እና የ5000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ።
በዚህ መሰረት በዛሬው እለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በሴቶች 5000 ማጣሪያ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና እጅጋየሁ ታዬ ኢትዮጵያን በመወከል የሚወዳደሩ አትሌቶች ናቸው።
የወንዶች 10000 ሜትር የፍጻሜ ውድድርም ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ላይ የሚካሄድ ሲሆን፤ ዮሚፍ ቀጀልቻ ፣ ሰለሞን ባረጋ እና በሪሁ አረጋዊ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።
በውሀ ዋና ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተወዳዳሪ አብዱልማሊክ ሙክታር በምድብ 3 ከቀኑ 7:28 ላይ በ50ሜትር ነፃ ቀዘፋ የመጀመሪያ ማጣሪያውን ያደርጋል።