በመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ የተመራው ልዑክ ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ተወያየ
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራው ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።
በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራውና የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ የተካተቱበት ልኡኩ ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ድረ ገፃቸው አስታውቀዋል።
ልዑኩ በአሜሪካ እያደረገ ያለው ጉብኝት የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
በውይይታቸው ስለተነሱ ነጥቦች ግን አምባሳደሩ በድረ ገፃቸው ያሉት ነገር የለም፡፡