አዲሷ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት በመጪው አርብ ኢትዮጵያ ይገባሉ
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንትነት ስራቸውን ህዳር 21/2012 ዓ.ም. በይፋ የጀመሩት ዩርሱላ ቮን ደ ሌይን የፊታችን አርብ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ብራሰልስ ታይምስ ዘግቧል፡፡
አዲሷ የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ስራ ከጀመሩ በኋላ ከአውሮፓ ውጭ የመጀመሪያ የሆነውን ጉብኝታቸውን ነው በአዲስ አበባ የሚያደርጉት፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃለ።
በመጪው እሁድ ጉብኝታቸውን በማጠናቀቅ ወደ ብራስልስ እንደሚመለሱም ዩርሱላ ቮን ደ ለይን ለብራሰልስ ታይምስ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቷ በቀጣዩ ሰኞ ደግሞ በ25ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ለውጥ ጉባኤ ላይ ለመታደም ስፔን ማድሪድ እንደሚያቀኑም በዘገባው ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡- ብራሰልስ ታይምስ